ኢሳይያስ 64:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 እሳት ጭራሮውን እንደሚያቃጥል፥ እሳትም ውኃውን እንደሚያፈላ፥ ስምህ ለጠላቶችህ እንዲገለጥ፥ አሕዛብም በፊትህ እንዲንቀጠቀጡ፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 እሳት ሲለኰስ ጭራሮን እንደሚያቀጣጥል፣ ውሃንም እንደሚያፈላ፣ ስምህ በጠላቶችህ ዘንድ እንዲታወቅ ውረድ፤ መንግሥታትም በፊትህ እንዲንቀጠቀጡ አድርግ! ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 እሳት ደረቁን እንጨት በሚያጋይ ጊዜ ፍሙ የተጣደውን ውሃ እንደሚያፍለቀልቀው፥ ሕዝቦችም በአንተ መገለጥ እንዲንቀጠቀጡ ወርደህ ስምህ በጠላቶችህ ዘንድ እንዲታወቅ አድርግ! ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 አደሮ ማር በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ እንዲሁ ጠላቶችህን እሳት ትበላቸዋለች፤ ስምህም በእነርሱ ላይ ይታወቃል፤ አሕዛብም በፊትህ ይደነግጣሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 እሳት ጭራሮውን እንደሚያቃጥል፥ እሳትም ውኃውን እንደሚያፈላ፥ ስምህ ለጠላቶችህ ይገለጥ ዘንድ፥ አህዛብም በፊትህ ይንቀጠቀጡ ዘንድ። ምዕራፉን ተመልከት |