ኢሳይያስ 60:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፤ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፥ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 የቄዳር የበግ መንጋ ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባል፤ የነባዮት አውራ በጎች ያገለግሉሻል። እነዚህም በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት የሚኖራቸው መሥዋዕቶች ይሆናሉ፤ እኔም የክብር መቅደሴን ግርማ አጐናጽፈዋለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 የቄዳር የበግ መንጋዎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ፤ የነባዮት አውራ በጎችም ለመሥዋዕትነት ያገለግሉሻል፤ በመሠዊያም ላይ ለመሥዋዕትነት ለመቅረብ ተቀባይነት ይኖራቸዋል። የተከበረውን ቤተ መቅደሴንም አስጌጣለሁ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 የቄዳር በጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ፤ የነባዮትም አውራ በጎች ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ በመሠዊያዬ ላይም የተመረጠው መሥዋዕት ይቀርባል፤ የጸሎቴ ቤትም ይከብራል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፥ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፥ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ። ምዕራፉን ተመልከት |