Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 60:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በቁጣዬ ቀሥፌ በፍቅሬ ምሬሻለሁና ባዕዳን ቅጥርሽን ይሠራሉ፤ ነገሥታቶቻቸውም ያገለግሉሻል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “ባዕዳን ቅጥሮችሽን ይሠራሉ፤ ነገሥታቶቻቸው ያገለግሉሻል፤ በቍጣዬ ብመታሽም፣ ርኅራኄዬን በፍቅር አሳይሻለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እኔ በቊጣዬ ቀጥቼሽ ነበር፤ አሁን ግን እራራልሻለሁ። ባዕዳን ሕዝቦች ቅጽሮችሽን ይሠራሉ፤ ንጉሦቻቸውም ያገለግሉሻል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በቍ​ጣዬ ቀሥፌ በይ​ቅ​ር​ታዬ አቅ​ር​ቤ​ሻ​ለ​ሁና መጻ​ተ​ኞች ቅጥ​ር​ሽን ይሠ​ራሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም በፊ​ትሽ ይቆ​ማሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በቍጣዬ ቀሥፌ በፍቅሬ ምሬሻለሁና መጻተኞች ቅጥርሽን ይሠራሉ፥ ነገሥታቶቻቸውም ያገለግሉሻል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 60:10
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መጻተኞችም ቆመው በጎቻችሁን ያሰማራሉ፥ ባዕዳንም አራሾችና ወይን ጠባቂዎች ይሆኑላችኋል።


ነገሥታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፥ እቴጌዎቻቸውም ሞግዝቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፥ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም ጌታ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።


የአሕዛብንም ግርማና ክብር ወደ እርሷ ያመጣሉ።


አሕዛብም በብርሃንዋ ይመላለሳሉ፤ የምድርም ነገሥታት ክብራቸውን ወደ እርሷ ያመጣሉ፤


በሩቅ ያሉትም መጥተው የጌታን መቅደስ ይሠራሉ፤ የሠራዊት ጌታም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። የአምላካችሁንም የጌታን ቃል በእውነት ብትታዘዙ ይህ ይሆናል።


አሕዛብም ወደ ብርሃንሽ፥ ነገሥታትም ወደ መውጫሽ ጸዳል ይመጣሉ።


በዚያን ቀን እንዲህ ትላለህ፤ “ጌታ ሆይ፤ ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤ አሁን ግን ከቁጣህ ተመለስህ፤ ደግሞም አጽናንተኸኛልና እወድስሃለሁ።


ቅዱሳን ሆይ፥ ለጌታ ዘምሩ፥ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ።


ካህናትና ሌዋውያን እንዲሆኑ ከእነርሱ እወስዳለሁ፥ ይላል ጌታ።


አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ለዘለዓለም ትኖራለህ፥ መታሰቢያህም ለልጅ ልጅ ነው።


ያገለግሉት ዘንድ የጌታንም ስም ለመውደድ አገልጋዮቹም ለመሆን ወደ ጌታ የሚጠጉትንም መጻተኞች፥ እንዳያረክሱት ሰንበትን የሚጠብቁትን፥ በቃል ኪዳኔኔም የሚጸኑትን ሁሉ፥


የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት፥ አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እንዳውጅ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ እንዳጽናና፥


አቤቱ ጌታ፥ እጅግ አትቈጣ፥ ለዘለዓለምም ኃጢአትን አታስብ፤ እነሆ፥ እባክህ፥ ተመልከት፥ እኛ ሁላችን ሕዝብህ ነን።


ጌታም ስለ ምድሩ ቀና፥ ለሕዝቡም ራራለት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች