Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 59:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል የመለያያ አጥር ሆናለች፤ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ነገር ግን በደላችሁ ከአምላካችሁ ለይቷችኋል፤ ኀጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል፤ በዚህም ምክንያት አይሰማም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በደላችሁ በእናንተና በእግዚአብሔር መካከል ሆኖ ጋረደ፤ ኃጢአታችሁ ከእግዚአብሔር ስለ ለያችሁ ጸሎታችሁ አይሰማም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ነገር ግን በደ​ላ​ችሁ በእ​ና​ን​ተና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መካ​ከል ለይ​ታ​ለች፤ ይቅ​ርም እን​ዳ​ይ​ላ​ችሁ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ ፊቱን ከእ​ና​ንተ ሰው​ሮ​ታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፥ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 59:2
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በደላችሁ እነዚህን አስቀርታለች፥ ኃጢአታችሁም መልካምን ነገር ከለከለቻችሁ።


ጌታ ከኀጥኣን ይርቃል፥ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል።


የዚያን ጊዜ ወደ ጌታ ይጮኻሉ፥ እርሱ ግን አይመልስላቸውም፤ በዚያን ጊዜ ፊቱን ከእነርሱ ይሰውራል፥ ሥራቸው ክፉ ነውና።


እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፤ ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤


ፊቴንም ከእነርሱ ከእንግዲህ ወዲህ አልሰውርም፥ መንፈሴን በእስራኤል ቤት ላይ አፍስሻለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ኃጢአት ስለ ሞላበት ስግብግብነቱ ተቈጣሁት፤ ቀጣሁት፤ ፊቴንም በቁጣ ከእርሱ ሰወርኩ፤ እርሱ ግን በመንገዱ ገፋበት።


እስራኤል ኃጢአት ሠርቶአል፤ ያዘዝኋቸውንም ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል፤ እርም የሆነውንም ነገር ወሰዱ፥ ሰረቁም፥ ዋሹም፥ በዕቃቸውም ውስጥ ሸሸጉት።


እነሆ፥ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ፤ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ፤ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ለማሰማት ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ እናታችሁን የፈታሁበት የፍቺዋ ጽሕፈት የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለየትኛው ነው? እነሆ፥ ስለ ኃጢአታችሁ ተሸጣችኋል፥ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈታለች።


ሔት። ኢየሩሳሌም እጅግ ኃጢአት ሠርታለች፥ ስለዚህ ረክሳለች፥ ያከብሩአት የነበሩ ሁሉ ኀፍረተ ሥጋዋን አይተዋታልና አቃለሉአት፥ እርሷም እየጮኸች ታለቅሳለች ወደ ኋላም ዘወር አለች።


ሠራዊቱ ወደ ሰፈር በተመለሰ ጊዜ የእስራኤል አለቆች፥ “ዛሬ ጌታ በፍልስጥኤማውያን እንድንሸነፍ ያደረገን ለምንድን ነው? አብሮን እንዲወጣ፥ ከጠላቶቻችንም እጅ እንዲያድነን የጌታን የኪዳኑን ታቦት ከሴሎ እናምጣ” አሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች