Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 58:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በዚያን ጊዜ በጌታ ደስ ይልሃል፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፥ የአባትህንም የያዕቆብን ርስት አበላሃለሁ፤ ይህን የጌታ አፍ ተናግሮአልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በዚያ ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፤ በምድር ከፍታዎች ላይ እንድትጋልብ፣ የአባትህን የያዕቆብን ርስት ጠግበህ እንድትበላ አደርግሃለሁ።” የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሯልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በእኔ በእግዚአብሔር ደስ ይላችኋል፤ በምድርም ላይ ከፍ ባለ ቦታ እንድትኖሩ አደርጋለሁ፤ ለቀድሞ አባታችሁ ለያዕቆብ ካወረስኩት ርስት በሚገኘው ምርት እንድትጠግቡ አደርጋችኋለሁ። ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በዚ​ያን ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትታ​መ​ና​ለህ፤ በም​ድ​ርም በረ​ከት ላይ ያወ​ጣ​ሃል፤ የአ​ባ​ትህ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንም ርስት ይመ​ግ​ብ​ሃል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ እን​ደ​ዚህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፥ የአባትህንም የያዕቆብን ርስት አበላሃለሁ፥ የእግዚአብሔር አፍ ተናግሮአልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 58:14
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የዚያን ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል፥ ፊትህንም ወደ እግዚአብሔር ታነሣለህ።


ሁሉንስ በሚችል አምላክ ደስ ይለዋልን? እግዚአብሔርንስ ሁልጊዜ ይጠራልን?


ምድራቸውንም ርስት አድርጎ ለእስራኤል ለሕዝቡ ርስት ሰጠ።


ምድራቸውን ርስት አድርጎ የሰጠውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥


አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህን እንዴት አበዛህ! የሰው ልጆች በክንፎችህ ጥላ ይታመናሉ።


ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፥ በብዙም ሰላም ደስ ይላቸዋል።


በጌታ ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።


እርሱ ከፍ ባለ ሥፍራ ይቀመጣል፤ ጠንካራ አምባ መጠጊያው ይሆናል፤ እንጀራም ይሰጠዋል፥ ውኃውም የማታቋርጥ ትሆናለች።


በጌታ መጽሐፍ ፈልጉ አንብቡም፤ የጌታ አፍ አዝዞአልና፥ መንፈሱ ሰብስቦአቸዋልና ከእነዚህ አንዲት አትጠፋም፥ ጥንዱን የሚያጣ የለም።


ከዚያም የጌታ ክብር ይገለጣል፥ ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፥ የጌታ አፍ ይህን ተናግሮአል።”


አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።


እኔ ግን፦ “‘ከወንዶች ልጆች ጋር እንዴት አስቀምጥሻለሁ? ያማረችውንስ ምድር እጅግ የከበረችውን የአሕዛብን ርስት እንዴት እሰጥሻለሁ? ብዬ ነበር። ደግሞ፦ አባቴ ብለሽ ትጠሪኛለሽ፤ እኔንም ከመከተል አትመለሽም ብዬ ነበር።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠላት በእናንተ ላይ፦ “እሰይ! የጥንት ከፍታዎች ለእኛ ርስት ሆነዋል” ብሏልና፥


እያንዳንዱ ሰው ከወይኑና ከበለሱ በታች ይቀመጣል፥ የሚያስፈራውም የለም፤ የሠራዊት ጌታ አፍ ተናግሮአልና።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


“በምድር ከፍታ ላይ አወጣው፥ የምድሩንም ፍሬ በላ፤ ከዓለትም ድንጋይ ማር፥ ከባልጩትም ድንጋይ ዘይት መገበው።


እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፥ በጌታ የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው? እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥ የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህም ይገዙልሃል፥ አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ።”


ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፤ ደስ ይበላችሁ።


እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩትም በእርሱ በማመናችሁ መግለጽ በማይቻልና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ብሎአችኋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች