Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 56:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሰንበቴን ለሚጠብቁ፥ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ለሚመርጡ፥ ቃል ኪዳኔንም ለሚይዙ ጃንደረቦች፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰንበቶቼን ለሚያከብሩ ጃንደረቦች፣ ደስ የሚያሠኘኝን ለሚመርጡ፣ ቃል ኪዳኔን፣ ለሚጠብቁ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰንበቴን ለሚያከብሩ፥ እኔ የምፈቅደውን ነገር ለሚመርጡና፥ በቃል ኪዳኔ ለሚጸኑ ጃንደረቦች

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጃ​ን​ደ​ረ​ቦች እን​ዲህ ይላል፥ “ሰን​በ​ቴን ቢጠ​ብቁ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ኝ​ንም ነገር ቢመ​ርጡ፥ በቃል ኪዳ​ኔም ጸን​ተው ቢኖሩ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 56:4
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁሉንም ነገር አዘጋጅቶና ጠብቆ፥ ከእኔ ጋር ዘላለማዊ ኪዳን ያደረገ፥ መዳኔን ከፍጻሜ የሚያደርሰው፥ መሻቴን ሁሉ የሚሰጠኝ እርሱ አይደለምን? በውኑ ቤቴ በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ አይደለምን?


የልቤ ደስታ ነውና ምስክርህን ለዘለዓለም ወረስሁ።


የጌታ መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ነው ቃል ኪዳኑንና ምስክሩን ለሚጠብቁ።


ይህ ካልሆነ ግን ጉልበቴን ለእርዳታ ይያዝ፥ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርግ፤ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርግ።


ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ሰውነታችሁ በሕይወት እንድትኖር ስሙኝ፥ የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።


ይህን የሚያደርግ ሰው ይህንንም የሚይዝ የሰው ልጅ፥ እንዳያረክሰው ሰንበትንም የሚጠብቅ እጁንም ክፋት ከማድረግ የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።


ያገለግሉት ዘንድ የጌታንም ስም ለመውደድ አገልጋዮቹም ለመሆን ወደ ጌታ የሚጠጉትንም መጻተኞች፥ እንዳያረክሱት ሰንበትን የሚጠብቁትን፥ በቃል ኪዳኔኔም የሚጸኑትን ሁሉ፥


ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ፥ እግርህን ወደ ሰንበት፥ ሰንበትንም ደስታ፥ ጌታንም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፥ በራስህ መንገድህን ከመጓዝ፥ ፈቅድህንም ከመፈጸም፥ ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፥


ፊታቸውንም ወደዚያ አቅንተው፦ ኑ፥ ከቶ በማይረሳ በዘለዓለም ቃል ኪዳን ከጌታ ጋር በአንድነት እንሁን፥ ብለው ወደ ጽዮን የሚወስደውን መንገድ ይጠይቃሉ።


የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ማርያምም መልካሙን ድርሻ መርጣለች፤ ከእርሷም አይወሰድባትም።”


ስለዚህም እግዚአብሔር የተስፋውን ቃል ለሚወርሱ ፈቃዱ እንደ ማይለወጥ አብልጦ ሊያሳያቸው ስለ ፈቀደ፥ በመሓላ በመካከል ገባ፤


ጌታንም ማገልገል ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ አባቶቻችሁ በወንዝ ማዶ ሳሉ ያገለገሉአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው የተቀመጣችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታገለግሉ እንደሆነ፥ የምታገለግሉትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን ጌታን እናገለግላለን።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች