Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 54:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 አታፍሪምና አትፍሪ፤ አትዋረጂምና አትደንግጪ፤ የሕፃንነትሽንም እፍረት ትረሺዋለሽ፥ የመበለትነትሽንም ስድብ ከእንግዲህ ወዲህ አታስቢም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 “አይዞሽ አትፍሪ፤ ኀፍረት አይገጥምሽም፤ ውርደት ስለማይደርስብሽ አትሸማቀቂ፤ የወጣትነት ኀፍረትሽን ትረሺዋለሽ፤ የመበለትነት ስድብሽንም ከእንግዲህ አታስታውሺውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ኀፍረትም ሆነ ውርደት ስለማይደርስብሽ አትፍሪ፤ በወጣትነትሽ ጊዜ የደረሰብሽን ኀፍረት ትረሺአለሽ፤ ባልዋ እንደ ሞተባት ሴት ብቸኛ ሆነሽ ያሳለፍሽውን የስድብ ዘመን አታስታውሺም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 አታ​ፍ​ሪ​ምና አት​ፍሪ፤ አቷ​ረ​ጂ​ምና አት​ደ​ን​ግጪ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም እፍ​ረ​ት​ሽ​ንም ትረ​ሺ​ዋ​ለሽ፤ የመ​በ​ለ​ት​ነ​ት​ሽ​ንም ስድብ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አታ​ስ​ቢም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 አታፍሪምና አትፍሪ፥ አትዋረጂምና አትደንግጪ፥ የሕፃንነትሽንም እፍረት ትረሺዋለሽ፥ የመበለትነትሽንም ስድብ ከእንግዲህ ወዲህ አታስቢም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 54:4
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መከራህንም ትረሳለህ፥ እንዳለፈ ውኃ ታስበዋለህ።


ሞትን ለዘለዓለም ይውጣል፥ ጌታ እግዚአብሔር ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፥ የሕዝቡንም ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ ይህን ጌታ ተናግሮአል።


ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠ ጌታ ስለ ያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፦ ያዕቆብ አሁን አያፍርም፥ ፊቱም አሁን አይለወጥም።


በዚያን ቀን ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው፤ “የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤ የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤ በአንተ ስም ብቻ እንጠራና፤ ውርደታችንን አስቀርልን” ይሉታል።


እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳሀለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።


አንተ ትል ያዕቆብ፥ ታናሽ እስራኤል ሆይ፥ አትፍራ፤ እረዳሃለሁ፥ ይላል ጌታ፥ የሚቤዥህም የእስራኤል ቅዱስ ነው።


ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛልና አልታወክሁም፤ ስለዚህም ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌዋለሁ፥ ኀፍረት ላይ እንደማልወድቅም አውቃለሁ።


ጽድቅን የምታውቁ ሕጌም በልባችሁ ያለ ሕዝብ ሆይ፥ ስሙኝ፤ የሰውን ተግዳሮት አትፍሩ፥ በስድባቸውም አትደንግጡ።


በጽድቅ ትታነጺያለሽ፤ ከግፍ ራቂ፥ አትፈሪምም፥ ድንጋጤም ወደ አንቺ አይቀርብም።


በኀፍረታችሁ ፈንታ ሁለት እጥፍ ይሆንላችኋል፤ በውርደታችሁም ፋንታ ዕድል ፋንታችሁ ደስ ይለዋል፤ ስለዚህ የምድራቸውን ሁለት እጥፍ ይገዛሉ፥ የዘለዓለምም ደስታ ይሆንላቸዋል።


እንዲሁም በምድር ላይ የተባረከ በእውነት አምላክ ይባረካል፥ በምድርም ላይ የማለ በእውነት አምላክ ይምላል፤ ምክንያቱም የቀድሞው ጭንቀት ተረስቶአል፥ ከዓይኔም ተሰውሮአል።


ከተመለስሁ በኋላ ተጸጸትሁ፥ ከተገሠጽሁም በኋላ በኀዘን ጭኔን ጸፋሁ፤ የብላቴንነቴንም ስድብ ተሸክሜአለሁና አፈርሁ ተዋረድሁም።’


አሌፍ። ሕዝብ ሞልቶባት የነበረች ከተማ ብቻዋን እንዴት ተቀመጠች! በአሕዛብ መካከል ታላቅ የነበረች እንደ መበለት ሆናለች፥ በአውራጆች መካከል ልዕልት የነበረች ተገዢ ሆናለች።


በርኩሰቶችሽ ሁሉና በአመንዝራነትሽ ዕርቃንሽን ሆነሽ ተራቁተሽም በደምሽ ውስጥ ስትንፈራገጪ የነበርሽበት የልጅነትሽን ጊዜ አላስታወስሺም።


በእነዚህ ነገሮች ሁሉ አስቆጣሽኝ እንጂ የልጅነትሽን ወራት አላስታወስሺም፤ ስለዚህ እነሆ እኔ ደግሞ መንገድሽን በራስሽ ላይ እመልሳለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ በርኩሰቶችሽ ሁሉ ላይ ሌላ ነውር አትጨምሪም።


ዳግመኛም የአሕዛብን ውርደት አላሰማብሽም፥ ዳግመኛም የአሕዛብን ስድብ አትሸከሚም፥ ዳግመኛም ሕዝብሽን አታሰናክዪም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ምድር ሆይ፥ ጌታ ታላቅ ነገር አድርጎአልና አትፍሪ፥ ደስም ይበልሽ፥ እልልም በዪ።


በዚያ ቀን በእኔ ላይ አምፀሽ በሠራሽው ሥራ ሁሉ አታፍሪም፤ በኩራትሽ የተደሰቱትን ከመካከልሽ አወጣለሁና፥ አንቺም በቅዱስ ተራራዬ ላይ ዳግመኛ አትታበዪም።


የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፥ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፤ ስለምራራላቸው ወደ ቦታቸው እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም በእኔ እንዳልተተዉ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው ጌታ ነኝና፥ እኔም እሰማቸዋለሁ።


ምክንያቱም በመጽሐፍ “እነሆ፥ የተመረጠና ክቡር የማእዘን ድንጋይ፥ በጽዮን አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም፤” ተብሎ ተጽፎአልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች