Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 53:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፤ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ በርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እርሱ ግን ተወግቶ የቈሰለው ስለ መተላለፋችን ነው፤ የደቀቀውም ስለ በደላችን ነው፤ እኛ የዳንነው እርሱ በተቀበለው ቅጣት ነው፤ በእርሱም ቊስል እኛ ተፈወስን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እርሱ ግን ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ቈሰለ፤ ስለ በደ​ላ​ች​ንም ታመመ፤ የሰ​ላ​ማ​ች​ንም ተግ​ሣጽ በእ​ርሱ ላይ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ቍስል እኛ ተፈ​ወ​ስን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፥ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 53:5
27 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ክርስቶስ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኃጢአት መከራን ተቀበለ፤ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርባችሁ በሥጋ ሞተ፥ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።


የሰው ልጅም ሊያገለግል፥ ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”


እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን ስለ እኛ ኃጢአት የሌለበትን እርሱን ኃጢአት አደረገው።


ምክንያቱም አንድ ጊዜ ራሱን መሥዋዕት በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋል።


ስለ ኃጢአታችን ለሞት ተላልፎ ተሰጠ፤ ለጽድቃችንም ተነሣ።


በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በማቅረብ ተቀድሰናል።


እኔ የተቀበልሁትንና ከሁሉ በላይ የሆነውን ለእናንተ አስተላልፌአለሁ፤ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚሉት ክርስቶስ ለኀጢአታችን ሞተ፤


እንዲሁም ክርስቶስ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ተሰውቷል። ለሁለተኛ ጊዜ ሲታይ ሊያድናቸው ለሚጠባበቁት ኃጢአትን ለመሸከም ሳይሆን መዳንን ለማምጣት ነው።


ክርስቶስም እንዳፈቀራችሁ፥ ስለ እናንተም ለእግዚአብሔር መልካም መዓዛ ያለው መባንና መሥዋዕት አድርጎ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ፥ በፍቅር ተመላለሱ።


“በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ “በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፥ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”


ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ በጎቹም እንዲበተኑ እረኛውን ምታ፤ እጄንም በታናናሾች ላይ አዞራለሁ።


ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤


የጌታ አምላክህን ተግሣጽ ይኸውም ግርማውን፥ ብርቱ እጁንና የተዘረጋች ክንዱን ያዩትና የተለማመዱት ልጆቻችሁ ሳይሆኑ እናንተ እንደ ሆናችሁ ዛሬ አስታውሱ፤


አቤቱ፥ ተቀብለኸኛልና፥ ጠላቶቼንም ደስ አላሰኘህብኝምና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።


የሰንበር ቁስል ክፉዎችን ያነጻል፥ ግርፋትም ወደ ሆድ ጉርጆች ይገባል።


አፌንም በእሳቱ ነክቶ፤ “እነሆ፤ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህ ተወግዶልሃል፤ ኃጢአትህም ተሰርዮልሃል” አለኝ።


ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ፤ የተቀጠረችበት ወራት እንደ ተፈጸመ፥ ኃጢአትዋም እንደ ተሰረየ፥ ከጌታም እጅ ስለ ኃጢአትዋ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች ወደ እርሷ ጩኹ።


መንገዶቹን አይቻለሁ፤ ቢሆንም እፈውሰዋለሁ፤ እመራዋለሁ፤ ለእርሱና ስለ እርሱ ለሚያለቅሱትም መጽናናትን እሰጣለሁ።


እየራራለት፦ እሱን መታደጊያ ቤዛ አግኝቻለሁና ወደ መቃብር እንዳይወርድ አድነው ቢለው፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች