Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 52:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ያልተነገረላቸውን ያያሉና፥ ያልሰሙትንም ያስተውላሉና ነገሥታት ስለ እርሱ አፋቸውን ይዘጋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ስለዚህ ብዙ መንግሥታትን ያስደንቃል፤ በርሱ ምክንያት ነገሥታት አፋቸውን ይይዛሉ፤ ያልተነገራቸውን ያያሉ፤ ያልሰሙትንም ያስተውላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ቀድሞ ያልተነገራቸውን ነገር ስለሚያዩና ያልሰሙትን ነገር ስለሚያስተውሉ ብዙ ሕዝቦች ስለ አገልጋዬ ይደነቃሉ፤ ነገሥታትም በእርሱ በመደነቅ የሚናገሩትን ያጣሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ እር​ሱን ያደ​ን​ቃሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ትም አፋ​ቸ​ውን ይዘ​ጋሉ፤ ስለ እርሱ ያል​ተ​ወ​ራ​ላ​ቸው ያው​ቁ​ታ​ልና፥ ያል​ሰ​ሙ​ትም ያስ​ተ​ው​ሉ​ታ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ያልተነገረላቸውን ያያሉና፥ ያልሰሙትንም ያስተውላሉና ነገሥታት ስለ እርሱ አፋቸውን ይዘጋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 52:15
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእስራኤል ታዳጊ ቅዱሱም፥ ጌታ፥ ሰዎች በሚንቁት ሕዝብም ለሚጠላው፥ ለገዢዎች አገልጋይ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ ታማኙ ስለ ጌታ ስለ መረጠህም ስለ እስራኤል ቅዱስ ነገሥታት አይተው ይነሣሉ፥ መሳፍንትም አይተው ይሰግዳሉ።’


እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ ያወቃችሁ፥ በመንፈስ የተቀደሳቹ፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ትታዘዙና በደሙም ትረጩ ዘንድ ለተመረጣችሁት፥ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።


ስለዚህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ፥ በወልድና መንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤


በእናንተ ላይ ንጹሕ ውኃ እረጫለሁ እናንተም ትነጻላችሁ፥ ከርኩሰቶቻችሁ ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አነጻችኋለሁ።


እነሆ፥ የማታውቀውን ሕዝብ ትጠራለህ፥ የእስራኤልም ቅዱስ አክብሮሃልና ስለ አምላክህ ስለ ጌታ የማያውቅህ ሕዝብ ወደ አንተ ይሮጣል።


ነገሥታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፥ እቴጌዎቻቸውም ሞግዝቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፥ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም ጌታ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።


የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።


የበኩር ልጆችን የሚያጠፋው እንዳይነካቸው ፋሲካን የጠበቀውና ደምን መርጨትን ያደረገው በእምነት ነበር።


ከክፉ ኅሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተንና ሰውነታችንን በንጹህ ውሃ ታጥበን፥ በቅን ልብ በፍጹም እምነት እንቅረብ፤


ስለዚህ በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ብሎና የመንፈስ ቅዱስን የተስፋ ቃል ከአብ ተቀብሎ ይህን እናንተ አሁን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው።


እነሆ፥ እጄን በላያቸው ላይ አነሣለሁ፥ በምርኮ ተገዝተውላቸው ለነበሩት ራሳቸው በምርኮ ይዘረፋሉ፤ የሠራዊት ጌታም እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።


ጽድቄ ፈጥኖ ቀርቦአል፥ ማዳኔም ወጥቶአል፥ ክንዴም በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፤ ደሴቶች እኔን በመተማመን ይጠባበቃሉ፥ በክንዴም ይታመናሉ።


“እነሆ፥ እኔ ወራዳ ሰው ነኝ፥ የምመልስልህ ምንድነው? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ።


እነርሱንም ለማንጻት እንዲህ ታደርግላቸዋለህ፤ ኃጢአትን የሚያነጻውን ውኃ እርጫቸው፥ በገላቸውም ላይ ያለውን ጠጉር ሁሉ በምላጭ ይላጩ፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፥ ራሳቸውንም ንጹሕ ያድርጉ።


ንጹሕም ሰው ሂሶጱን ወስዶ በውኃው ውስጥ ይነክረዋል፤ በድንኳኑም፥ በዕቃውም ሁሉ፥ በዚያም ባሉ ሰዎች ላይ፥ ዐፅሙንም ወይም የተገደለውን ወይም የሞተውን ወይም መቃብሩን በነካው ሰው ላይ ይረጨዋል፤


ወደ እኔ ተመልከቱ፥ ተደነቁም፥ እጃችሁንም በአፋችሁ ላይ አኑሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች