ኢሳይያስ 51:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ስለ ወገኑ የሚምዋገት አምላክሽ ጌታሽ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የሚያንገደግድን ጽዋ የቁጣዬንም ዋንጫ ከእጅሽ ወስጃለሁ፤ ደግመሽም ከእንግዲህ ወዲህ አትጠጪውም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ሕዝቡን የሚታደግ አምላክሽ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ከእጅሽ፣ ያንገደገደሽን ጽዋ ወስጃለሁ፤ ያን ጽዋ፣ የቍጣዬን ዋንጫ፣ ዳግም አትጠጪውም፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 የሕዝቡን አቤቱታ የሚመለከተው አምላካችሁ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እንደ ሰከረ ሰው የሚያንገዳግደውን የመከራ ጽዋ ከእጃችሁ ወስጄአለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ኀይለኛ ቊጣዬን ከትልቁ ዋንጫ አትጠጡም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ለወገኑ የሚፈርድ አምላክሽ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ የሚያንገደግድሽን ጽዋ የቍጣዬንም ጽዋ ከእጅሽ ወስጃለሁ፤ ደግመሽም ከእንግዲህ ወዲህ አትጠጪውም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ስለ ወገኑ የሚምዋገት አምላክሽ ጌታሽ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የሚያንገደግድን ጽዋ የቍጣዬንም ዋንጫ ከእጅሽ ወስጃለሁ፥ ደግመሽም ከእንግዲህ ወዲህ አትጠጪውም። ምዕራፉን ተመልከት |