Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 51:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እነዚህ ሁለት ነገሮች ሆነውብሻል፥ ማንስ ያስተዛዝንሻል? መፈታትና ጥፋት፥ ራብና ሰይፍ ናቸው፤ እንዴትስ አድርጌ አጽናናሻለሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እነሆ፤ በጥፋት ላይ ጥፋት መጥተውብሻል፤ ታዲያ ማን ያጽናናሻል? እነርሱም መፈራረስና ጥፋት፣ ራብና ሰይፍ ናቸው፤ ታዲያ ማን ያስተዛዝንሽ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ውድመትና ጥፋት፥ ራብና ጦርነት፥ እነዚህ ሁለት ነገሮች ደርሰውብሻል፤ የሐዘንሽ ተካፋይ የሚሆን ማነው? ማንስ ያጽናናሻል?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 አሁ​ንም እነ​ዚህ ሁለቱ ይጠ​ብ​ቁ​ሻል፤ ማን ያስ​ተ​ዛ​ዝ​ን​ሻል? እነ​ር​ሱም ጥፋ​ትና ውድ​ቀት ራብና ሰይፍ ናቸው፤ እን​ግ​ዲህ የሚ​ያ​ጽ​ና​ናሽ ማን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እነዚህ ሁለት ነገሮች ሆነውብሻል፥ ማንስ ያስተዛዝንሻል? መፈታትና ጥፋት ራብና ሰይፍ ናቸው፥ እንዴትስ አድርጌ አጽናናሻለሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 51:19
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየአገራቸው መጡ፥ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው ቢልዳድ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊያዝኑለትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ ለመምጣት ተስማሙ።


ወንድሞቹና እኅቶቹ ቀድሞም ያውቁት የነበሩት ሁሉ ወደ እርሱ መጡ፥ በቤቱም ከእርሱ ጋር እንጀራ በሉ፥ ስለ እርሱም አዘኑለት፥ ጌታም ካመጣበት ክፉ ነገር ሁሉ አጽናኑት፥ እያንዳንዳቸውም ብርና የወርቅ ቀለበት ሰጡት።


አንተ ስድቤን እፍረቴንም ነውሬንም ታውቃለህ፥ የሚያስጨንቁኝ ሁሉ በፊትህ ናቸው።


እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፥ እነሆም፥ የተገፉት ሰዎች እንባ፥ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፥ በሚገፉአቸውም እጅ ኃይል ነበረ፥ እነርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።


የድሆችም የበኩር ልጆች ይሰማራሉ፥ ችግረኞችም ተዘልለው ይተኛሉ፤ ሥርህንም በራብ እገድላለሁ፥ ቅሬታህም ይገደላል።


ስለዚህ፦ “ከእኔ እራቁ፤ መራራ ልቅሶ ላልቅስበት፤ ስለ ሕዝቤ ጥፋት ልታጽናኑኝ አትድከሙ” አልኩ።


አሁን ግን እነዚህ ሁለት ነገሮች፥ የወላድ መካንነትና መበለትነት፥ በአንድ ቀን በድንገት ይመጡብሻል፤ ምንም መተት ብታበዥና ምንም ዓይነት አስማት ቢኖርሽም ፈጽሞ አይቀሩልሽም።


አንቺ የተሸገርሽ በአውሎ ነፋስም የተናወጥሽ ያልተጽናናሽም፥ እነሆ፥ ድንጋዮችሽን ሸላልሜ እገነባለሁ፥ በሰንፔርም እመሠርትሻለሁ።


ከዚያ በኋላ በምድርሽ ውስጥ ግፍ፥ በዳርቻሽም ውስጥ ጉስቁልናና ቅጥቃጤ አይሰማም፤ ቅጥርሽን መዳን በሮችሽንም ምስጋና ብለሽ ትጠሪያለሽ።


የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት፥ አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እንዳውጅ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ እንዳጽናና፥


ተጨንቀውና ተርበው በምድሪቱ ላይ ይንከራተታሉ፤ ክፉኛ ሲራቡም ይቈጣሉ፤ ወደ ላይ እየተመለከቱ ንጉሣቸውንና አምላካቸውን ይራገማሉ።


ምናሴ ኤፍሬምን፤ ኤፍሬም ምናሴን ይበላል፤ በይሁዳም ላይ በአንድነት ይነሣሉ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።


“ኢየሩሳሌም ሆይ! የሚራራልሽ ማን ነው? የሚያዝንልሽስ ማን ነው? ወይስ ስለ ደኅንነትሽ ቆም ብሎ የሚጠይቅ ማነ ነው?


ለእነርሱና ለአባቶቻቸውም ከሰጠኋቸው ምድር እስኪጠፉ ድረስ በመካከላቸው ሰይፍንና ራብን ቸነፈርንም እልክባቸዋለሁ።”


ላሜድ። እናንተ መንገድ አላፊዎች ሁሉ፥ በእናንተ ዘንድ ምንም የለምን? እግዚአብሔር በጽኑ ቁጣው ቀን እኔን እንዳስጨነቀበት በእኔ ላይ እንደተደረገው እንደ እኔ መከራ የሚመስል መከራ እንዳለ ተመልከቱ፥ እዩ።


ጤት። አደፍዋ በልብስዋ ዘርፍ ነበረ፥ ፍጻሜዋን አላሰበችም፥ ስለዚህ በድንቅ ተዋርዳለች፥ የሚያጽናናትም የለም፥ አቤቱ፥ ጠላት ከፍ ከፍ ብሏልና መከራዬን ተመልከት።


ድንጋጤና ቁጣ፥ ጥፋትና ቅጥቃጤ ሆነብን።


ክፉ አውሬ በምድሪቱ እንዲያልፍ ባደርግ፥ ልጅ አልባ ቢያደርጋት፥ በአውሬው ምክንያት ማንም እንዳያልፍባት ባድማ ብትሆን፥


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ላይ አራቱን ክፉ ፍርዶቼን ሰይፍ፥ ራብ፥ ክፉ አውሬና ቸነፈር፥ ሰውንና እንስሳን ከእርሷ ለማጥፋት ብሰድድም፥


የምድሩንም እጽዋት በልተው ከጨረሱ በኋላ፥ እኔ፦ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ ያዕቆብ ታናሽ ነውና እንዴት ይቆማል?” አልሁ።


የሚያይሽም ሁሉ ከአንቺ ሸሽቶ፦ ነነዌ ወድማለች፤ ማን ያዝንላታል? አንቺን የሚያጽናኑ ከወዴት እፈልጋለሁ? ይላል።


ስለዚህ ተጽናንተናል፤ ክመጽናናታችንም ሌላ ስለ ቲቶ ደስታ እጅግ ደስ ብሎናል፤ ምክንያቱም ልቡ በሁላችሁም እረፍት አግኝቷል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች