Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 51:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አይሞትም ወደ ጉድጓድም አይወርድም፥ እንጀራም አይጐድልበትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ዐንገታቸውን የደፉ እስረኞች በፍጥነት ነጻ ይወጣሉ፤ በታሰሩበትም ጕድጓድ ውስጥ አይሞቱም፤ እንጀራ አያጡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እስረኞች በፍጥነት ነጻ ይወጣሉ፤ አይሞቱም፤ ወደ ጥልቁ ጒድጓድም አይወርዱም። የሚበሉትንም እንጀራ አያጡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ከዳ​ንሽ በኋላ እን​ግ​ዲህ አይ​ኖ​ር​ምና፥ አይ​ዘ​ገ​ይ​ም​ምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 አይሞትም ወደ ጕድጓድም አይወርድም፥ እንጀራም አይጐድልበትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 51:14
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከባቢሎን ውጡ ከከለዳውያንም ኰብልሉ፤ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፥ ይህንንም ንገሩ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩ፦ “ጌታ ባርያውን ያዕቆብን ታድጎታል!” በሉ።


ለአንቺ ደግሞ በቃል ኪዳንሽ ደም፥ እስረኞችሽን ውኃ ከሌለበት ጉድጓድ አውጥቻለሁ።


ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ትቢያን አራግፊ፤ ተነሺ፥ ተቀመጪ፤ ምርኮኛይቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የአንገትሽን እስራት ፍቺ።


የሚራራላቸውም ይመራቸዋልና፥ በውኃም ምንጮች በኩል ይነዳቸዋልና አይራቡም፥ አይጠሙም፥ የበረኅ ትኩሳት ወይም ፀሐይ አይጐዳቸውም።


እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሣሣው የይሁዳና የብንያም የአባቶች አለቆች፥ ካህናቱና ሌዋውያኑም ሁሉ ለመሄድና በኢየሩሳሌም ያለውን የጌታን ቤት ለመሥራት ተዘጋጁ።


ኤርምያስም በጉድጓድ ውስጥ ለውኃ ማከማቻ ወደሚሆን ቤት ወደ ጓዳዎቹ ገባ፤ እርሱም በዚያ ብዙ ቀን ከተቀመጠ በኋላ፥


የዘመንህም ጸጥታ የመድኃኒት፥ የጥበብና የእውቀት ብዛት ይሆናል፤ ጌታን መፍራት ሀብቱ ነው።


ጌታም የጭንቀትን እንጀራና የመከራን ውኃ ቢሰጥህም አስተማሪህ እንግዲህ ከአንተ አይሰወርም፤ ዐይኖችህ ግን አስተማሪህን ያያሉ፥


ጌታ ግን እንዲህ ይላል፦ ከአንቺ ጋር የሚጣሉትን እጣላቸዋለሁ፥ ልጆችሽንም አድናለሁና፥ በኃያላን የተማረኩ እንኳን ይወሰዳሉ፥ የጨካኞች ብዝበዛም ቢሆን ያመልጣል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች