Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 50:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የሚያጸድቀኝ ቅርብ ነው፤ ከእኔስ ጋር የሚከራከር ማን ነው? በአንድነት እንቁም፤ የሚከራከረኝ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅረብ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የሚያጸድቀኝ በአጠገቤ አለ፤ ታዲያ ማን ሊከስሰኝ ይችላል? እስኪ ፊት ለፊት እንጋጠም! ተቃዋሚዬስ ማን ነው? እስኪ ይምጣ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የሚፈርድልኝ እግዚአብሔር ቅርብ ነው፤ ታዲያ ማን ይከሰኛል? የሚከሰኝ ካለ ፊት ለፊት እንገናኝ፤ እስቲ ይቋቋመኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የሚ​ያ​ጸ​ድ​ቀኝ ቅርብ ነው፤ ከእ​ኔስ ጋር የሚ​ከ​ራ​ከር ማን ነው? እስቲ በእኔ ላይ ይነሣ፤ የሚ​ከ​ራ​ከ​ረ​ኝስ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅ​ረብ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የሚያጸድቀኝ ቅርብ ነው፥ ከእኔስ ጋር የሚከራከር ማን ነው? በአንድነት እንቁም፥ የሚከራከረኝ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅረብ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 50:8
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእኔስ ጋር የሚፋረድ ማን ነው? አሁን እኔ ዝም ብል እሞታለሁ።


አቤቱ፥ አንተ ቅርብ ነህ፥ መንገዶችህም ሁሉ ቅኖች ናቸው።


አንድ ሰው ለባልንጀራው አህያ ወይም በሬ ወይም በግ ወይም ሌላ እንስሳ እንዲጠብቅለት በአደራ ቢሰጥ፥ ማንም ሳያይ ቢሞት ወይም ቢጎዳ ወይም ቢማረክ፥


“ኑና፤ እንዋቀስ” ይላል ጌታ፤ “ኀጢአታችሁ እንደ ዐለላ ቢቀላ እንደ በረዶ ይነጣል፤ እንደ ደም ቢቀላም እንደ ባዘቶ ነጭ ይሆናል።


ደሴቶች ሆይ፥ በፊቴ ዝም በሉ፤ አሕዛብም ኃይላቸውን ያድሱ፤ ይቅረቡም በዚያን ጊዜም ይናገሩ፤ ለፍርድ በአንድነት እንቅረብ።


ሙግታችሁን ይዛችሁ ቅረቡ፥ ይላል ጌታ፤ ማስረጃችሁን አምጡ፥ ይላል የያዕቆብ ንጉሥ።


አሳስበኝ፥ በአንድነትም ሆነን እንፋረድ፤ እንድትጸድቅ ነገርህን ተናገር።


የእስራኤልም ዘር ሁሉ በጌታ ይጸድቃሉ፥ ይመካሉም ይከብራሉም።


በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም የሚነሣብሽን ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የጌታ አገልጋዮች ርስት ይህ ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል ጌታ።


ባላጋራህ ለዳኛ፥ ዳኛውም ለሎሌው እንዳይሰጥህ ወደ እስር ቤት እንዳትገባ፤ ከባላጋራህ ጋር በመንገድ አብረኸው ስትሄድ ሳለህ ፈጥነህ ተስማማ፤


ሁለቱም ወገኖች በጌታ ፊት፥ በዚያ ወቅት በሚያገለግሉት ካህናትና ፈራጆች ፊት ይቁሙ።


የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም፦ በሥጋ ተገለጠ፥ በመንፈስ ጸደቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ በአሕዛብ መካከል ተሰበከ፥ በመላው ዓለም ታመነ፥ በክብር ዐረገ፥ የሚል ነው።


ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ፤ እንዲህ ሲል “አሁን የአምላካችን ማዳን፥ ኃይልም፥ መንግሥትም እንዲሁም የክርስቶስ ሥልጣን ሆነ፤ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች