ኢሳይያስ 5:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ጆሮዬ እየሰማ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “ታላላቅ ቤቶች ወና ይቀራሉ፤ የሚያማምሩም ቤቶች ነዋሪ ያጣሉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ጆሮዬ እየሰማ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “ታላላቅ ቤቶች ወና ይቀራሉ፣ የሚያማምሩም ቤቶች ኗሪ ያጣሉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 እነሆ የሠራዊት አምላክ እንዲህ ብሎ በመሐላ ሲያረጋግጥ ሰምቼአለሁ፦ “የተዋቡ ታላላቅ ቤቶች ሁሉ ፈርሰው ወና ይሆናሉ፤ የሚኖርባቸው ሰውም አይገኝም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ይህ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ጆሮ ተሰምቶአልና፦ ቤቶች ቢሠሩ ባድማ ይሆናሉ፤ ታላላቅና የሚያምሩ ቤቶችም የሚቀመጥባቸው አይኖርም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጆሮዬ እንዲህ አለ፦ በእውነት ብዙ ታላቅና መልካም ቤት ባድማ ይሆናል፥ የሚቀመጥበትም አይገኝም። ምዕራፉን ተመልከት |