Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 49:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 “ጌታ እንዲህ ይላል፦ በተወደደ ጊዜ ሰምቼሃለሁ፥ በመዳንም ቀን ረድቼሃለሁ፤ እጠብቅሃለሁ፥ ምድርንም እንድታቀና፥ ውድማ የሆኑትንም ርስቶች እንድታወርስ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በተወደደ ጊዜ እመልስልሃለሁ፤ በድነት ቀን እረዳሃለሁ። ለሕዝቡ ቃል ኪዳን እንድትሆን፣ ምድሪቱን እንደ ገና እንድትሠራት፣ ጠፍ የሆኑትን ርስቶች ለየባለቤታቸው እንድትመልስ፣ እጠብቅሃለሁ፤ እሠራሃለሁም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በመረጥኩት ሰዓት ለጸሎትህ መልስ እሰጥሃለሁ፤ በመዳንም ቀን እረዳሃለሁ፤ ምድሪቱን መልሰህ እንድታቋቋምና ውድማ የሆነውን መሬት እንድታከፋፍል ቃል ኪዳን አድርጌ ለሕዝቡ ሰጥቼሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በተ​መ​ረ​ጠ​ችው ዕለት ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ድኅ​ነት በሚ​ደ​ረ​ግ​በ​ትም ቀን ረድ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ቃል ኪዳን አድ​ርጌ ለሕ​ዝቡ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ምድ​ር​ንም ታቀና ዘንድ፥ ውድማ የሆ​ኑ​ትን ርስ​ቶች ትወ​ርስ ዘንድ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በተወደደ ጊዜ ሰምቼሃለሁ፥ በመድኃኒትም ቀን ረድቼሃለሁ፥ እጠብቅህማለሁ፥ ምድርንም ታቀና ዘንድ፥ ውድማ የሆኑትንም ርስቶች ታወርስ ዘንድ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 49:8
31 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱ፥ “በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ፤ በመዳንም ቀን ረዳሁህ፤” ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳንም ቀን አሁን ነው።


እኔ ጌታ በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፤ እጅህንም እይዛለሁ፤ እጠብቅሃለሁ፤ ለሕዝቡ ቃል ኪዳን፤ ለአሕዛብም ብርሃን አደርግሃለሁ።


በደጅ የሚቀመጡ በእኔ ይጫወታሉ፥ ሰካራሞች በእኔ ላይ ይዘፍናሉ።


የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።


ከጥንትም ጀምሮ ባድማ የነበሩትን ይሠራሉ፥ ከቀድሞ የፈረሱትንም ያቆማሉ፤ ባድማ የነበሩትንና ከብዙ ትውልድ በፊት የፈረሱትን ከተሞች እንደገና ይሠራሉ።


ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፥ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል፤ አንተም፦ ሰባራውን ጠጋኝ፥ የአውራ መንገድ አዳሽ ትባላለህ።


እርሱም ሥጋ ለብሶ በምድር በሚመላለስ ጊዜ፥ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል፥ ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ስለ ጻድቅ ፍርሃቱም ጸሎቱ ተሰማለት፤


ሰማያትን እንድዘረጋ ምድርንም እንድመሠርት፥ ጽዮንንም፦ “አንቺ ሕዝቤ ነሽ” እንድል ቃሌን በአፍህ አድርጌአለሁ፥ በእጄም ጥላ ጋርጄሃለሁ።


የባርያዬን ቃል አጸናለሁ፤ የመልእክተኞቼንም ምክር እፈጽማለሁ፤ ኢየሩሳሌምን፦ የሰው መኖሪያ ትሆኛለሽ፥ የይሁዳንም ከተሞች፦ ትታነጻላችሁ ፍራሾቻችሁንም አቆማለሁ እላለሁ።


በውድ ልጁም በነጻ የሰጠን የከበረ ጸጋው እንዲመሰገን ይህን አደረገ።


በቀኝና በግራ ትስፋፊያለሽ፥ ዘርሽም አሕዛብን ይወርሳሉ፥ የፈረሱትንም ከተሞች መኖሪያ ያደርጋሉ።


ባድማሽና ውድማሽ ወናም የሆነው ምድርሽ ከሚኖሩብሽ የተነሣ ዛሬ ጠባብ ትሆናለችና፥ የዋጡሽም ይርቃሉ።


እነሆ ደግፌ የያዝሁት አገልጋዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፤ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል።


በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ በአንተ ላይ ታምናለችና በሰላም ትጠብቃታለህ።


“በወሰንኩት ጊዜ እኔ በቅን እፈርዳለሁ።”


ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ።


አሁን ግን በተሻለ ተስፋ ቃል ስለ ተመሠረተ፥ መካከለኛ የሆነበት ኪዳን የተሻለ እንደሆነ ሁሉ፥ የተቀበለውም አገልግሎት ከእነርሱ አገልግሎት ይበልጣል፥፥


ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የኪዳን ደሜ ይህ ነው።


ጌታም ጽዮንን ያጽናናል፤ በእርሷም ባድማ የሆነውን ሁሉ ያጽናናል፤ ምድረ በዳዋንም እንደ ዔድን በረሀዋንም እንደ ጌታ ገነት ያደርጋል፤ ደስታና ተድላ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ ይገኝበታል።


ለስሜ ቤት የሚሠራ እርሱ ነው፤ እኔም የመንግሥቱን ዙፋን ለዘለዓለም አጸናለሁ።


እኔ ጌታ ጠባቂው ነኝ፤ ሁልጊዜ ውሃ አጠጣዋለሁ፤ ማንም እንዳይጎዳው በሌሊትና በቀን እጠብቀዋለሁ።


እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳሀለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።


ጌታ በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤


ወደ አንቺ የሰበሰብሻቸው በጮኽሽ ጊዜ ይታደጉሽ፤ ንፋስ ግን ይወስዳቸዋል፤ ሽውሽውታም ሁሉን ያስወግዳቸዋል። በእኔ የታመነ ግን ምድሪቱን ይገዛል፥ የተቀደሰውንም ተራራዬን ይወርሳል።


እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነው? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነው? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ እንዲያደርግ፥ ማቅንና አመድንም በበታቹ እንዲያነጥፍ ነው? በውኑ ይህን ጾም፥ በጌታ ዘንድ የተወደደ ቀን ብለህ ትጠራዋለህ?


የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት፥ አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እንዳውጅ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ እንዳጽናና፥


ከያዕቆብም ዘርን ከይሁዳም ተራሮቼን የሚወርሰውን አወጣለሁ፤ እኔም የመረጥኳቸው ይወርሷታል፥ አገልጋዬቼም በዚያ ይኖራሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች