ኢሳይያስ 48:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 እናንተ ሁሉ፥ በአንድነት ተሰብስባችሁ ስሙ፤ ከእነርሱ ይህን የተናገረ ማን ነው? ጌታ የወደደው ፈቃዱን በባቢሎን ላይ ያደርጋል፥ ክንዱም በከለዳውያን ላይ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 “ሁላችሁም በአንድነት ተሰብሰቡ፤ አድምጡም፤ ከጣዖቶች አስቀድሞ እነዚህን የተናገረ ማን ነው? የእግዚአብሔር ምርጥ ወዳጅ የሆነ፣ እርሱ በባቢሎን ላይ ያቀደውን እንዲፈጽም ያደርገዋል፤ ክንዱም በባቢሎናውያን ላይ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 “ሁላችሁም ተሰብስባችሁ ኑና አድምጡ! ስለ እነዚህ ነገሮች አስቀድሞ የተናገረ ከጣዖቶች መካከል የትኛው ነው? የእግዚአብሔር ተመራጭ በባቢሎን ላይ ዓላማውን ይፈጽማል። ኀይሉም በባቢሎናውያን ላይ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ሁሉም በአንድነት ተሰብስበው ይሰማሉ፤ ይህን ማን ነገራቸው? አንተን በመውደድ የከለዳውያንን ዘር አስወግድ ዘንድ ፈቃድህን በባቢሎን ላይ አደረግሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 እናንተ ሁሉ፥ በአንድነት ተሰብስባችሁ ስሙ፥ ከእነርሱ ይህን የተናገረ ማን ነው? እግዚአብሔር የወደደው ፈቃዱን በባቢሎን ላይ ያደርጋል፥ ክንዱም በከለዳውያን ላይ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከት |