Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 47:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴንም አረከስሁ፤ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ከእነርሱ ጋር ምሕረት አላደረግሽም፤ በሽማግሌዎቻቸው ላይ ቀንበርሽን እጅግ አክብደሻል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሕዝቤን ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴን አርክሼው ነበር፤ አሳልፌ በእጅሽ ሰጠኋቸው፤ አንቺ ግን አልራራሽላቸውም፤ በዕድሜ በገፉት ላይ እንኳ፣ እጅግ ከባድ ቀንበር ጫንሽባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እኔ በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ እነርሱንም እንደ ርኩስ ቈጥሬ፥ ለአንቺ አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ አንቺ ግን ርኅራኄ አላደረግሽላቸውም፤ በዕድሜ በገፉት ሰዎች ላይ የጭቈና ቀንበር አበዛሽባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በሕ​ዝቤ ላይ ተቈ​ጥቼ ነበር፤ ርስ​ቴ​ንም አረ​ከ​ስሽ፤ በእ​ጅ​ሽም አሳ​ልፌ ሰጠ​ኋ​ቸው፤ ለሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸው አል​ራ​ራ​ሽም፤ ቀን​በ​ራ​ቸ​ው​ንም እጅግ አክ​ብ​ደ​ሻል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር ርስቴንም አረከስሁ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፥ ከእነርሱ ጋር ምሕረት አላደረግሽም፥ በሽማግሌዎቻቸው ላይ ቀንበርሽን እጅግ አክብደሻል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 47:6
28 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊትም ጋድን፥ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ምሕረቱ ብዙ ነውና በጌታ እጅ እንውደቅ፤ በሰው እጅ ግን አልውደቅ” አለው።


አሁንም አባቴ ከባድ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፥ እኔ ግን በቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችሁ ነበር፥ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ።’ ”


በዚያም ዖዴድ የተባለ የጌታ ነቢይ ነበረ፤ ወደ ሰማርያም የሚመጣውን ጭፍራ ሊገናኘው ወጣ፥ እንዲህም አላቸው፦ “እነሆ፥ የአባቶቻችሁ አምላክ ጌታ ይሁዳን ስለ ተቈጣ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጣቸው፥ እናንተም ወደ ሰማይ በሚደርስ ቁጣ ገደላችኋቸው።


ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጉልማሶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጎልማሳውንና ድንግሊቱን ሽማግሌውንና አዛውንቱን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።


ከሰይፍም ያመለጡትን ወደ ባቢሎን ማረካቸው፤ የፋርስ ንጉሥም እስኪነግሥ ድረስ ለንጉሡና ለልጆቹ ባርያዎች ሆኑ፤


ነገር ግን አባቶቻችን የሰማያትን አምላክ ስላስቆጡት በከለዳዊው በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ እርሱም ይህን ቤት አፈረሰ፥ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ።


ማደሪያቸው በረሃ ትሁን፥ በድንኳኖቻቸውም የሚቀመጥ አይገኝ፥


ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፤ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፤ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፤ አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፤ በሚያስቆጣኝም ሕዝብ ላይ እሰደዋለሁ።


ዐይናቸው እያየ ሕፃናታቸው ይጨፈጨፋሉ፤ ቤታቸው ይዘረፋል፤ ሚስቶቻቸው ይደፈራሉ።


ዓለሙን ባድማ ያደረገ፥ ከተሞችንም ያፈረሰ፥ ምርኮኞቹንም ወደ ቤታቸው ያልላከ ሰው ይህ ነውን? ብለው ያስተውሉሃል።


ሕዝቦችንም በማያቋርጥ ቁጣ የመታውን፥ ያለ ርኅራኄ ያለማቋረጥ ቀጥቅጦ አሕዛብን በማይበርድ ቁጣው የገዛውን ሰብሮአል።


ስለዚህ የመቅደሱን አለቆች አረከስኩ፥ ያዕቆብንም እርግማን፥ እስራኤልንም ስድብ አደረግሁ።


ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ፤ ጨካኞች ናቸው ምሕረትም አያደርጉም፤ ድምፃቸው እንደ ባሕር የሚተምም ነው፤ በፈረሶች ላይ ይቀመጣሉ፤ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ! ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ሰው እያንዳንዳቸው በአንቺ ላይ ተሰለፉ።


ኖን። የኃጢአቶቼ ቀንበር በእጁ ተይዛለች፥ ታስረው በአንገቴ ላይ ወጥተዋል፥ ጉልበቴን አደከመ። ጌታ በፊታቸው እቆም ዘንድ በማልችላቸው እጅ አሳልፎ ሰጠኝ።


ሳን። እኔ እየጮኽሁ እንደማለቅስ ሰምተዋል፥ የሚያጽናናኝ የለም፥ ጠላቶቼ ሁሉ ስለ መከራዬ ሰምተዋል፥ አንተ አድርገኸዋልና ደስ አላቸው፥ ስለ እርሱ የተናገርኸውን ቀን ታመጣለህ እነርሱም እንደ እኔ ይሆናሉ።


ቤት። ጌታ የያዕቆብን ማደሪያዎች ሁሉ ዋጠ፥ አልራራምም፥ በመዓቱ የይሁዳን ሴት ልጅ አምቦች አፈረሰ፥ ወደ ምድርም አወረዳቸው መንግሥቱንና አለቆችዋን አረከሰ።


ዔ። የእግዚአብሔር ፊት በተናቸው እርሱም ከእንግዲህ ወዲህ አይመለከታቸውም፥ የካህናቱን ፊት አላፈሩም፥ ሽማግሌዎቹንም አላከበሩም።


አለቆች በእጃቸው ተሰቀሉ፥ የሽማግሌዎች ፊት አልታፈረም።


ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የኃይላችሁ ትምክሕት፥ የዓይናችሁ ምኞት፥ የነፍሳችሁ ናፍቆት የሆነውን መቅደሴን አረክሳለሁ፤ ትታችኋቸው የሄዳችሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።


በንግድህ ብዛት ግፍ በውስጥህ ተሞላ ኃጢአትንም ሠራህ፤ ስለዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ፤ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፥ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አጠፋሁህ።


በወንድምህ በያዕቆብ ላይ ስለተደረገው ግፍ እፍረትን ትከናነባለህ፤ ለዘለዓለምም ትጠፋለህ።


በቅዱስ ተራራዬ ላይ እንደ ጠጣችሁ እንዲሁ አሕዛብ ሁሉ ዘወትር ይጠጣሉ፥ አዎን፥ ይጠጣሉ፥ ይጨልጡማል፥ እንዳልሆኑም ይሆናሉ።


የጌታም መልአክ መልሶ፦ “አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ፥ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን የኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው?” አለ።


እኔ ብዙም ሳልቆጣቸው እነርሱ ክፋትን ስላገዙት፥ በምቾት በሚኖሩት አሕዛብ ላይ እጅግ ተቈጥቻለሁ።


በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋል፤ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።


እርሱም ሽማግሌ የማያከብርና ለብላቴና የማይራራ፥ ሲያዩት የሚያስፈራ ሕዝብ ነው።


ምሕረት ያላደረገ ሁሉ ያለ ምሕረት ይፈረድበታልና፤ ምሕረትም ፍርድን ያሸንፋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች