ኢሳይያስ 45:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 እኔ ምድርን ሠርቻለሁ ሰውንም በእርሷ ላይ ፈጥሬአለሁ፤ እኔ በእጄ ሰማያትን ዘርግቻለሁ፥ ሠራዊታቸውንም ሁሉ አዝዣለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ምድርን የሠራሁ እኔ ነኝ፤ ሰውንም በላይዋ ፈጥሬአለሁ፤ እጆቼ ሰማያትን ዘርግተዋል፤ የሰማይንም ሰራዊት አሰማርቻለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ምድርን የፈጠርኩና ሰውንም ፈጥሬ በእርስዋ እንዲኖር ያደረግኹ እኔ ነኝ፤ ሰማያትን በኀይሌ የዘረጋሁና ሠራዊቶቻቸውን የምቈጣጠር እኔ ነኝ።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 እኔ ምድርን ሠርቻለሁ፤ ሰውንም በእርስዋ ላይ ፈጥሬአለሁ፤ እኔ በእጄ ሰማያትን አጽንቼአለሁ፤ ከዋክብቶቻቸውንም ሁሉ አዝዣለሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 እኔ ምድርን ሠርቻለሁ ሰውንም በእርስዋ ላይ ፈጥሬአለሁ፥ እኔ በእጄ ሰማያትን ዘርግቻለሁ፥ ሠራዊታቸውንም ሁሉ አዝዣለሁ። ምዕራፉን ተመልከት |