ኢሳይያስ 42:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ወደ ባሕር የምትወርዱ በእርሷም ውስጥ ያላችሁ ሁሉ፥ ደሴቶችና በእነርሱም ላይ የምትኖሩ፥ ለጌታ አዲስ መዝሙር፥ ከምድርም ዳርቻ ምስጋናውን ዘምሩ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 እናንተ ወደ ባሕር የምትወርዱ፣ በዚያም ያላችሁ ሁሉ፣ ደሴቶችና በዚያ የምትኖሩ በሙሉ፣ ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር፣ ከምድር ዳርቻም ምስጋናውን ዘምሩ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ! የዓለም ሕዝቦች ሁሉ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ! በባሕሩ ውስጥ ያሉት ሁሉ፥ የጠረፍ አገሮችና በእነርሱም የሚኖሩ ሁሉ ያመስግኑ! ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ወደ ባሕር የምትወርዱ፥ በእርስዋም ውስጥ የምትጓዙ ሁሉ፥ ደሴቶችና በእነርሱም ላይ የምትኖሩ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ፤ ከምድርም ዳርቻ ስሙን አክብሩ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ወደ ባሕር የምትወርዱ በእርስዋም ውስጥ ያላችሁ ሁሉ፥ ደሴቶችና በእነርሱም ላይ የምትኖሩ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር፥ ከምድርም ዳርቻ ምስጋናውን ዘምሩ። ምዕራፉን ተመልከት |