ኢሳይያስ 41:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 አናጢውም አንጥረኛውን፥ በመዶሻም የሚያሳሳውን በመስፍ ላይ የሚቀጠቅጠውን ያጽናናዋል፥ ስለ ብየዳ ሥራውም፦ “መልካም ነው” ይለዋል፤ እንዳይላቀቅም በችንካር ያጋጥመዋል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 የእጅ ጥበብ ባለሙያው የወርቅ አንጥረኛውን ያበረታታዋል፤ በመዶሻ የሚያሳሳውም፣ በመስፍ ላይ የሚቀጠቅጠውን ያነቃቃዋል፤ ስለ ብየዳም ሥራው፣ “መልካም ነው” ይለዋል፤ የጣዖቱ ምስል እንዳይወድቅም በምስማር ያጣብቀዋል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 የእጅ ጥበብ ዐዋቂው ወርቅ አንጥረኛን ያበረታታዋል፤ ጣዖት ጠርቦ በመዶሻ የሚያለሰልሰውም በመስፍ ላይ የሚመታውን ‘አይዞህ በርታ! ብየዳው መልካም ነው!’ ይለዋል። እንዳይንቀሳቀስም ጣዖቱን በምስማር ይቸነክሩታል።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 አናጢውም አንጥረኛውን፥ በመዶሻም የሚያሳሳውን መስፍ መችውን አጽናና፤ ስለ ማጣበቅ ሥራውም፥ “መልካም ነው” አለ፤ እንዳይንቀሳቀስም በችንካር አጋጠመው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 አናጢውም አንጥረኛውን፥ በመዶሻም የሚያሳሳውን መስፍ መችውን አጽናና፥ ስለ ማጣበቅ ሥራውም፦ መልካም ነው አለ፥ እንዳይንቀሳቀስም በችንካር አጋጠመው። ምዕራፉን ተመልከት |