Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 40:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤል ሆይ፦ “መንገዴ ከጌታ ተሰውራለች፥ ፍርዴም በአምላኬ ቸል ተብላለች” ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ያዕቆብ ሆይ፤ ለምን እንዲህ ትላለህ? እስራኤል ሆይ፤ ለምን እንዲህ ትናገራለህ? “መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች፤ ፍርዴም በአምላኬ ቸል ተብላለች” ለምን ትላለህ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 የያዕቆብ ዘር የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! “አካሄዴ ከእግዚአብሔር የተሰወረ ነው፤ መብቴም በእርሱ ዘንድ ችላ ተብሎብኛል፤” ብለህ ለምን ታማርራለህ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ያዕ​ቆብ ሆይ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሆይ፥ መን​ገዴ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተሰ​ው​ራ​ለች፤ አም​ላ​ኬም ከእኔ ርቋል፤ ፍር​ዴ​ንም ትት​ዋል፤ ለምን ትላ​ለህ? ለም​ንስ እን​ዲህ ትና​ገ​ራ​ለህ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤል ሆይ፦ መንገድህ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 40:27
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በእኔ ላይ የወሰነውን ይፈጽማል፥ እንደዚህ ያሉ ብዙ ብያኔዎች እንዳሉት።


“ፍርዴን ያስቀረ ሕያው እግዚአብሔርን! ነፍሴንም ያስመረራት ሁሉን የሚችል ሕያው አምላክን!


ኢዮብ፦ እኔ ንጹሕ ነኝ፥ እግዚአብሔር ግን ፍርድ ከለከለኝ፥


አቤቱ ጌታ፥ አንተ አምላኬ ነህ፤ አስቀድሞ የታሰበውን፤ ድንቅ ነገር በታማኝነትና በእውነት አድርገሃልና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ ስምህንም አመሰግናሁ።


ያዕቆብ ሆይ፥ አንተም እስራኤል፥ አገልጋዬ ነህና ይህን አስብ፤ እኔ ሠርቼሃለሁ አንተም አገልጋዬ ነህ፤ እስራኤል ሆይ፥ በእኔ ዘንድ ያልተረሳህ ትሆናለህ።


ጽዮን ግን፦ “ጌታ ትቶኛል፥ እርሱ ረስቶኛል” አለች።


እኔ ግን፦ “በከንቱ ደከምሁ፥ ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ጉልበቴን ፈጀሁ፤ ፍርዴ ግን በጌታ ዘንድ፥ ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው” አልኩ።


በጥቂት ቁጣ ለቅጽበተ ዐይን ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፥ በዘለዓለምም ቸርነት እምርሻለሁ፥ ይላል ታዳጊሽ ጌታ።


ዳዊት በልቡ፦ “ከእነዚህ ቀናት በአንዱ በሳኦል እጅ መገደሌ ስለማይቀር፥ የሚበጀኝ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር መሸሽ ብቻ ነው፤ ከዚያ በኋላም ሳኦል በእስራኤል ሁሉ እኔን ማሳደዱን ይተዋል፤ እኔም ከእጁ አመልጣለሁ” ብሎ አሰበ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች