ኢሳይያስ 38:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 እነሆ፥ በአካዝ የጥላ ስፍራ ሰዓት መቁጠሪያ ላይ በደረጃዎች ያለውን ከፀሐይ ጋር የወረደውን ጥላ በዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደርጋለሁ። ፀሐይም በጥላው የሰዓት ስፍራ ላይ በወረደበት ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመለሰ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 በአካዝ የሰዓት መቍጠሪያ ደረጃ ላይ፣ የወረደውን የፀሓይ ጥላ በዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደርጋለሁ።’ ” ስለዚህ ወርዶ የነበረው የፀሓይ ጥላ ያንኑ ያህል ወደ ኋላ ተመለሰ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ንጉሥ አካዝ ባሠራው የመወጣጫ ደረጃ ላይ የሚያርፈውን ጥላ እግዚአብሔር እንደገና ዐሥር ደረጃዎችን አልፎ ወደ ኋላ እንዲመለስ ያደርገዋል።” ጥላውም ዐሥር ደረጃዎችን አልፎ ወደ ኋላ ተመለሰ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 እነሆ፥ በአባትህ የጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ ከፀሐይ ጋራ የወረደውን በደረጃዎች ያለውን ጥላ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደርጋለሁ።” ፀሐይም በጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ የወረደበት ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመለሰ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 እነሆ፥ በአካዝ የጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ ከፀሐይ ጋር የወረደውን በደረጃዎች ያለውን ጥላ አሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደርጋለሁ። ፀሐይም በጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ የወረደበት አሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመለሰ። ምዕራፉን ተመልከት |