Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 38:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ማደሪያዬ ተነቀለች፥ እንደ እረኛ ድንኳንም ከእኔ ዘንድ ተወገደች፤ ሕይወቴንም እንደ ሸማኔ ጠቀለልኩት፤ እርሱም ከመጠቅለያው ይቈርጠኛል፤ ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ፍጻሜዬን አቀረብከው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ቤቴ እንደ እረኛ ድንኳን ተነቀለ፤ ከእኔም ተወሰደ፤ ሕይወቴን እንደ ሸማኔ ጠቀለልሁ፤ ከመጠቅለያ ቈርጦኛል፤ ከጧት እስከ ማታ ልትጨርሰኝ ፈጠንህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሕይወቴ በድንገት እንደ እረኛ ድንኳን የተነቀለና የተጠቀለለ፥ ተሠርቶም ሳያልቅ ከሸማኔው መጠቅለያ እንደ ተቈረጠ ልብስ ሆነ ብዬ አስቤ ነበር፤ እግዚአብሔር ሕይወቴን በአጭር የቀጫት መስሎኝ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የቀ​ረ​ው​ንም ኑሬ​ዬን አጣሁ። ከእ​ኔም ወጣች፥ ተለ​የ​ችም። ድን​ኳ​ኑን ተክሎ እን​ደ​ሚ​ያ​ድ​ርና እን​ደ​ሚ​ሄድ፥ ሊቈ​ረጥ እንደ ተቃ​ረበ ሸማም እን​ዲሁ ነፍሴ በላዬ ሆነች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ማደሪያዬ ተነቀለች፥ እንደ እረኛ ድንኳንም ከእኔ ዘንድ ተወገደች፥ ሕይወቴንም እንደ ሸማኔ ጠቀለልሁ፥ እርሱም ከመጠቅለያው ይቈርጠኛል፥ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ታጠፋኛለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 38:12
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ፤ ይለወጣሉም፤ አንተ ግን አንተ ነህ፤ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም፤”


የምንኖርበት ምድራዊ ድንኳን የሆነው ሕይወት ቢፈርስ፥ በሰማይ ዘላለማዊ የሆነ በእጅ ያልተሠራ፥ በእግዚአብሔር የታነጸ መኖሪያ እንዳለን እናውቃለን።


ሁልጊዜም የተገረፍሁ ሆንሁ፥ መሰደቤም በማለዳ ነው።


ነገ የሚሆነውን አታውቁም። ሕይወታችሁ ምንድነው? ለጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት አይደላችሁምን?


በእውነትም የሚሞተው በሕይወት እንዲዋጥ፥ ጨምረን ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ የማንወድ ስለሆነ፥ በዚህ ድንኳን ሳለን ከብዶን እንቃትታለን።


በዘመናት ሁሉ የሚቀመጥባት አይኖርም፤ የሚቀመጥባትም የለም ዐረብ በዚያ ድንኳኑን አይተክልም፤ እረኛም መንጋውን በዚያ አያሳርፍም።


የጽዮን ሴት ልጅ በወይን አትክልት ውስጥ እንዳለ ዳስ፤ በዱባ ተክል ወስጥ እንደሚገኝ ጐጆ፤ እንደ ተከበበም ከተማ ተተወች።


መስፍኖች ደግሞ ተቀምጠው እኔን አሙኝ፥ አገልጋይህ ግን ሕግህን ያሰላስል ነበር።


ከቁጣህና ከመዓትህም የተነሣ፥ አንሥተኸኛልና፥ ጥለኸኝማልና።


በተከበበ ከተማ የሚያስደንቅ ምሕረቱን በእኔ የገለጠ ጌታ ይመስገን።


መንፈሴ ደከመ፥ ቀኖቼ አለቁ፥ መቃብርም ተዘጋጅቶልኛል።


እንደ አበባ ይፈካል፥ ይረግፋልም፥ እንደ ጥላም ይሸሻል፥ እርሱም አይጸናም።


እግዚአብሔርም ያደቀኝ ዘንድ፥ እጁንም ለቅቆ ያጠፋኝ ዘንድ ወድዶ ቢሆን ኖሮ!


በጥዋትና በማታ መካከል ይሰባበራሉ፥ ማንም ሳያስብ ለዘለዓለም ይጠፋሉ።


ታጥለቀልቃቸዋለህ፥ እንደ ሕልም ናቸው፥ በማለዳም እንደሚያልፍ ሣር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች