Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 36:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ስለ ሰረገሎችና ስለ ፈረሰኞች በግብጽ ስትታመን፥ ከአለቃዬ ባርያዎች የሚያንሰውን የአንዱን አለቃ ፊት ለመቃወም እንዴት ይቻልሃል?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የምትመካው በግብጽ ሠረገሎችና ፈረሶች ሆኖ ሳለ ከጌታዬ የበታች የጦር ሹማምት እንኳ አንዱን እንዴት መመለስ ትችላለህ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 አንተ ከአሦራውያን ባለሥልጣኖች የመጨረሻውን ዝቅተኛ መኰንን እንኳ ለመቋቋም የምትችል አይደለህም፤ ይህም ሆኖ ግብጻውያን ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን ይልኩልኛል ብለህ ተስፋ ታደርጋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ከታ​ና​ና​ሾቹ ከጌ​ታዬ አገ​ል​ጋ​ዮች የሚ​ያ​ን​ሰ​ውን የአ​ን​ዱን ጭፍራ ፊት መመ​ለስ እን​ዴት ትች​ላ​ለህ? ስለ ሰረ​ገ​ሎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች በግ​ብፅ የሚ​ታ​መኑ ለጌ​ታዬ ባሮች ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ስለ ሰረገሎችና ስለ ፈረሰኞች በግብጽ ስትታመን፥ ከጌታዬ ባሪያዎች የሚያንሰውን የአንዱን አለቃ ፊት ትቃወም ዘንድ እንዴት ይቻልሃል?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 36:9
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲህም ይል ነበር፤ “የጦር አዛዦቹ በሙሉ ነገሥታት አይደሉምን?


መንገድሽን ለመለወጥ ለምን በጣም ትሮጫለሽ? አሦር እንዳሳፈረሽ ግብጽ እንዲሁ ያሳፍርሻል።


እነሆ፥ በዚህ በተቀጠቀጠ የሸንበቆ በትር በግብጽ ተማምነሀል፤ ሰው ተማምኖ ቢመረኰዘው እጁን ወግቶ ያቈስለዋል፤ የግብጽ ንጉሥ ፈርኦን ለሚታመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው።


ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ ጌታ እጁን በሚዘረጋ ጊዜ፥ ረጂው ይሰናከላል ተረጂውም ይወድቃል፥ ሁሉም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።


የግብጽ እርዳታ ከንቱና ምንም ነው፤ ስለዚህ ስሙን፦ “በቤት የሚቀመጥ ረዓብ” ብዬ ጠርቼዋለሁ።


እነርሱም ከተስፋቸው ከኢትዮጵያ ከትምክሕታቸውም ከግብጽ የተነሣ ይፈራሉ፤ ያፍራሉም።


ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፥ ድል ግን ከጌታ ዘንድ ነው።


አንተ እኮ እጅግ በጣም ዝቅተኛ ከሆነው ከአሦር ተራ የጦር መኰንን ጋር እንኳ መወዳደር አትችልም፤ ግብጻውያን ሠረገሎችንና ፈረሶችን ይልኩልኛል ብለህ የምትጠባበቀውም በዚሁ ምክንያት ነው።


ንጉሡም ብዙ ፈረሶችን ለራሱ አያብዛ፤ ወይም ደግሞ ፈረሰኞች ለማብዛት ሕዝቡን ወደ ግብጽ አይመልስ፤ ጌታ፥ ‘በዚያ መንገድ ፈጽሞ አትመለሱ’ ብሎአችኋልና።


ይህም የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር ሶርያውያንን በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀበ የብዙ ሠራዊት ግሥጋሤ የሚመስል ድምፅ አሰምቶአቸው ስለ ነበር ነው፤ ይኸውም ሶርያውያን እንዳሰቡት የእስራኤል ንጉሥ የሒታውያንና የግብጽ ነገሥታትን ከነሠራዊቶቻቸው ቀጥሮ አደጋ ሊጥልባቸው የመጣ መስሎአቸው ነበር።


እንግዲህ አሁን ናና፥ ከአለቃዬ ከአሦር ንጉሥ ጋር ተደራደርና፥ የሚቀመጡባቸውንም ሰዎች ካገኘህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረሶች እሰጥሃለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች