Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 32:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እናንተ ዓለመኛ ሴቶች ሆይ፥ ተነሡ ድምፄንም ስሙ፤ እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ሴት ልጆች ሆይ፥ ንግግሬን አድምጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እናንተ ትዕቢት የወጠራችሁ ሴቶች፣ ተነሡ፤ ድምፄን ስሙ፤ እናንተ ተደላድላችሁ የምትኖሩ ሴቶች ልጆች ሆይ፤ የምነግራችሁን አድምጡ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እናንተ በምቾት የምትኖሩ ሴቶች ተነሥታችሁ ድምፄን ስሙ፤ እናንተ በኑሮአችሁ የምትተማመኑ ሴቶች ንግግሬን አድምጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እና​ንተ ባለ​ጸ​ጎች ሴቶች ሆይ፥ ተነሡ፤ ድም​ፄ​ንም ስሙ፤ እና​ንተ ተማ​ም​ና​ችሁ የም​ት​ቀ​መጡ ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ንግ​ግ​ሬን አድ​ምጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እናንተ ዓለመኞች ሴቶች ሆይ፥ ተነሡ ድምፄንም ስሙ፥ እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ንግግሬን አድምጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 32:9
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”


አድምጡ ድምፄንም ስሙ፤ ልብ አድርጉ ንግግሬንም ስሙ።


ጌታ እንዲህ ይላል፤ የጽዮን ሴቶች ኰርተዋል፤ ዐንገታቸውን እያሰገጉ፤ በዐይናቸውም እየጠቀሱ ይሄዳሉ፤ እየተቈነኑ በመራመድ፤ የእግራቸውን ዐልቦ ያቃጭላሉ።


ስጋት ሳይኖርባት የተቀመጠች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፥ በልብዋም፦ “እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ያለች፥ እንዴት አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ ሆነች! በእርሷ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፏጫል።


ሄ። የጣፈጠ ነገር ይበሉ የነበሩ በመንገድ ጠፉ፥ በቀይ ግምጃ ያድጉ የነበሩ የፍግ ክምር አቀፉ።


ኢዮአታም ይህ በተነገረው ጊዜ፥ በገሪዛን ተራራ ጫፍ ላይ ወጥቶ ድምጽን ከፍ በማድረግ እንዲህ አላቸው፤ የሴኬም ነዋሪዎች ሆይ፥ እግዚአብሔር ይሰማችሁ ዘንድ እኔን ስሙኝ፤


በመካከልህ ተለሳልሳና ተቀማጥላ የምትኖር፥ ከልስላሴና ከቅምጥልነት የተነሣ እግሮችዋ ዐፈር ነክቶት የማያውቁ ሴት ዐቅፋው ለምትተኛው ባሏና በገዛ ወንድ ወይም ሴት ልጆችዋ ላይ ትከፋለች።


የትምክሕተኞችን ሹፈትና የትዕቢተኞችን ንቀት ነፍሳችን እጅግ ጠገበች።


እናንተ ሴቶች ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ፥ ጆሮአችሁም የአፉን ቃል ትቀበል፥ ለሴቶች ልጆቻችሁም ልቅሶውን፥ እያንዳንዳችሁም ለባልንጀሮቻችሁ ዋይታውን አስተምሩ።


በጽዮን፦ ‘እንዴት ተበዘበዝን! ምድሪቱንም ትተናልና፥ ቤቶቻችንንም አፍርሰዋልና እንዴት አብዝተን አፈርን!’ የሚል የልቅሶ ድምፅ ተሰምቶአል።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች