Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 32:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ከእንግዲህ ወዲህ ሰነፍ ጨዋ ተብሎ አይጠራም፤ ሸንጋይ ሰው የተከበረ አይባልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከእንግዲህ ሰነፍ ጨዋ አይባልም፤ ጋጠወጥም አይከበርም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከእንግዲህ ወዲህ ሞኞች ጨዋዎች አይባሉም፤ ባለጌዎችም ክብር አይሰጣቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ሰነ​ፍን አለቃ ይሆን ዘንድ ግድ አይ​ሉ​ትም፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ሎሌህ ዝም በል አይ​ል​ህም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ከእንግዲህ ወዲህ ሰነፍ ከበርቴ ተብሎ አይጠራም፥ ንፉግም ለጋስ አይባልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 32:5
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ አንተ ጠብቀን፥ ከዚህችም ትውልድ ለዘለዓለም ታደገን።


ኃጢአተኛ ሰው በፊቱ የተናቀ፥ ጌታን የሚፈሩትን የሚያከብር፥ ቢጎዳም የማለውን የማይከዳ።


የሸንጋይ ሽንገላ ክፉ ናት፤ የችግረኛም አቤቱታ ትክክል ቢሆንም እንኳን በሐሰት ቃል ድሀውን ለማጥፋት ክፉን አሳብ ያስባል።


ክፉውን መልካም፤ መልካሙን ክፉ ለሚሉ ብርሃኑን ጨለማ፤ ጨለማውን ብርሃን ለሚያደርጉ፤ ጣፋጩን መራራ፤ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!


ተመልሳችሁም በጻድቁና በኃጢአተኛው መካከል፥ እግዚአብሔርን በሚያገለግለውና በማያገለግለው መካከል ያለውን ልዩነት ታያላችሁ።


ጌታዬ፥ ያን ባለጌ ሰው ናባልን ከቁምነገር አይቁጠረው፤ ስሙ ራሱ ሞኝ ማለት ስለሆነ፥ ሰውየውም ልክ እንደ ስሙ ነው፤ ሞኝነትም አብሮት የኖረ ነው። እኔ አገልጋይህ ግን ጌታዬ የላካቸውን ጐልማሶች አላየኋቸውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች