ኢሳይያስ 32:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ሴቶች ሆይ፥ ወይንን መቁረጥ ይጠፋልና፥ ፍሬም ማከማቸት አይመጣምና ከዓመትና ከጥቂት ቀን በኋላ ትንቀጠቀጣላችሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ዓመቱ ገና እንዳለፈ፣ ተደላድላችሁ የነበራችሁ ትንቀጠቀጣላችሁ፤ የወይን ተክል ፍሬ አይሰጥም፤ የፍራፍሬም ወቅት አይመጣም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 እናንተ በኑሮአችሁ የተማመናችሁ ሴቶች ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተስፋ የሚያስቈርጥ ጭንቀት ይደርስባችኋል፤ ከወይንም ሆነ ከሌላው ተክል ሁሉ በቂ ፍሬ አታገኙም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 በየዓመቱ የኀዘን በዓል መታሰቢያ አድርጉ፤ ወይን መቍረጥ አልፎአል፤ ፍሬ ማከማችትም አልቆአል፤ ከእንግዲህም ወዲህ አይመጣም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ሴቶች ሆይ፥ ወይንን መቍረጥ ይጠፋልና፥ ፍሬም ማከማቸት አይመጣምና ከዓመትና ከጥቂት ቀን በኋላ ትንቀጠቀጣላችሁ። ምዕራፉን ተመልከት |