Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 30:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ ይህችን ቃል አቃልላችኋልና፥ በግፍና በጠማምነት ታምናችኋልና፥ በእርሱም ተደግፋችኋልና፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ስለዚህ፣ የእስራኤል ቅዱስ እንዲህ ይላል፤ “ይህን ቃል ስላቃለላችሁ፣ ግፍን ስለ ታመናችሁ፣ ማታለልን ስለ ተደገፋችሁ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ ቃል ይህ ነው፦ “እናንተ ማስጠንቀቂያን ንቃችሁ ይደግፈናል ብላችሁ በተማመናችሁበት በግፍና በማታለል ላይ እምነታችሁን ጥላችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ እን​ዲህ ይላል፥ “ይህ​ችን ቃል አቃ​ል​ላ​ች​ኋ​ልና፥ በሐ​ሰ​ትና በጠ​ማ​ማ​ነት ተስፋ አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና፥ አጕ​ረ​ም​ር​ማ​ች​ኋ​ል​ምና፥ በዚ​ህም ቃል ታም​ና​ች​ኋ​ልና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ ይህችን ቃል አቃልላችኋልና፥ በግፍና በጠማምነት ታምናችኋልና፥ በእርሱም ተደግፋችኋልና

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 30:12
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያፈርስሃል፥ ከድንኳንም ይነቅልሃል ያፈልስሃልም፥ ሥርህንም ከሕያዋን ምድር።


ነገር ግን የሰው ልጆች ከንቱ ናቸው፥ የሰው ልጆችም ሐሰተኞች ናቸው፥ በሚዛንም ይበድላሉ፥ እነርሱስ በፍጹም ከንቱ ናቸው።


ልባቸው ግፍን ታስባለችና፥ ከንፈራቸውም ተንኮልን ትናገራለችና።


በምድር በሚኖሩት ላይ በበደላቸው ምክንያት ቁጣውን ሊያመጣባቸው፥ እነሆ፥ ጌታ ከስፍራው ይወጣል፤ ምድርም ያፈሰሰችውን ደም ትገልጣለች፥ የተገደሉትንም ከእንግዲህ ወዲህ አትሸሽግም።


እናንተም፦ “ከሞት ጋር ቃል ኪዳን አድርገናል፥ ከሲኦልም ጋር ተማምለናል፤ ሐሰትን መሸሸጊያችን አድርገናልና፥ በሐሰትም ተሰውረናልና የሚትረፈረፍ መቅሠፍት ባለፈ ጊዜ አይደርስብንም” ስላላችሁ፥


ጌታ ከአለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ጋር እንዲህ ሲል ይፋረዳል፤ “የወይኔን ቦታ ያጠፋችሁ እናንተ ናችሁ፤ ከድኾች የዘረፋችሁትም በቤታችሁ ይገኛል፤


ሕዝቤን በችግር ስታደቁት፤ የድኾችንም ፊት በኀዘን ስታገረጡት ምን ማለታችሁ ነው?” ይላል ጌታ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ለዓመፀኞች ልጆች ወዮላቸው! ይላል ጌታ፤ ከእኔ ዘንድ ያልሆነን ምክር ይመክራሉ፥ ኃጢአትንም በኃጢአት ላይ ለመጨመር ከመንፈሴ ያልሆነውን ቃል ኪዳን ያደርጋሉ።


የግብጽ እርዳታ ከንቱና ምንም ነው፤ ስለዚህ ስሙን፦ “በቤት የሚቀመጥ ረዓብ” ብዬ ጠርቼዋለሁ።


በክፋትሽ ታምነሻል፤ “የሚያየኝ የለም” ብለሻል፤ ጥበብሽና እውቀትሽ አታልለውሻል፥ በልብሽም፦ “እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ብለሻል።


ስለዚህ የእሳት ነበልባል ገለባን እንደሚበላ፤ ድርቆሽም በእሳት ጋይቶ እንደሚጠፋ፤ የእነርሱም ሥር እንዲሁ ይበሰብሳል፤ አበባቸውም እንደ ትቢያ ይበናል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋልና፤ የእስራኤል ቅዱስ የተናገረውንም ቃል አቃለዋል።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የወይን ቦታ የእስራኤል ቤት ነው፤ የይሁዳ ሰዎችም የደስታው አትክልት ናቸው። ፍትሕን ፈለገ፤ ነገር ግን ደም ማፍሰስን አየ፤ ጽድቅን ፈለገ፤ ነገር ግን የጭንቅን ጩኸት ሰማ።


ዐምፀናል፥ ሐሰትን ተናግረናል፥ ጌታን ከመከተል ተመልሰናል፤ ግፍንና ዓመፅንም ተናግረናል፥ የኃጢአት ቃልንም ፀንሰን ከልብ አውጥተናል።


በጽድቅ የሚጠራ በእውነትም የሚፈርድ የለም፤ በእርባና ቢስ ነገር ታምነዋል ሐሰትንም ተናግረዋል፤ ጉዳትን ፀንሰዋል በደልንም ወልደዋል።


የኤፍሬም ራስ ሰማርያ፤ የሰማርያም ራስ የሮሜልዩ ልጅ ነው። እንግዲህ በእምነታችሁ ካልጸናችሁ፤ ፈጽሞ መቆም አትችሉም።’


“ይህ ሕዝብ በጸጥታ የሚፈሰውን የሰሊሆምን ውሆች ትቶ፤ በረአሶንና በሮሜልዩ ልጅ ተደስቶአልና።


ረስተሽኛልና፥ በሐሰትም ታምነሻልና ዕጣሽ፥ የለካሁልሽም ድርሻሽ ይህ ነው፥ ይላል ጌታ።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “የጌታን ሕግ ጥለዋልና፥ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፥ አባቶቻቸውም የተከተሉአቸው ሐሰቶቻቸው አስተዋቸዋልና ስለ ሦስት የይሁዳ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።


“የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል፤ እናንተንም የማይቀበል እኔን አይቀበልም፤ እኔንም የማይቀበል የላከኝን አይቀበልም።”


ስለዚህ ይህን የማይቀበል፥ የማይቀበለው፥ ሰውን ሳይሆን፥ ቅዱስ መንፈሱን ደግሞም የሰጠንን እግዚአብሔርን ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች