Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 3:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ጀግናውንና ተዋጊውን፤ ፈራጁንና ነቢዩን፤ አስማተኛውንና ሽማግሌውን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ጀግናውንና ተዋጊውን፣ ፈራጁንና ነቢዩን፣ አስማተኛውንና ሽማግሌውን፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2-3 ጀግኖቻቸውን፥ ወታደሮቻቸውን፥ ዳኞቻቸውንና ነቢያታቸውን፥ ሟርተኞቻቸውንና ሽማግሌዎቻቸውን፥ የጦር መኰንኖቻቸውንና አማካሪዎቻቸውን፥ ጠንቋዮቻቸውንና የወደፊቱን እናውቃለን የሚሉትን ሁሉ ነቃቅሎ ያጠፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ኀያ​ሉ​ንም፥ ተዋ​ጊ​ው​ንም፥ ፈራ​ጁ​ንም፥ ነቢ​ዩ​ንም፥ ዐዋ​ቂ​ው​ንም፥ ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንም፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ኃያሉንም፥ ተዋጊውንም፥ ፈራጁንም፥ ነብዩንም፥ ምዋርተኛውንም፥ ሽማግሌውንም፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 3:2
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እስራኤልም ሁሉ በየትውልዳቸው ተቈጠሩ፤ እነሆም፥ በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጻፉ። ይሁዳም ስለ ኃጢአታቸው ወደ ባቢሎን ተማረኩ።


ምልክታችንን አናይም ከእንግዲህ ወዲህም ነቢይ አይኖርም፥ ይህም እስከ መቼ እንደሚቆይ የሚያውቅ በኛ ዘንድ የለም።


የአምሳ አለቃውንና ባለ ማዕረጉን፤ አማካሪውንና ጠቢቡን የእጅ ባለሙያ፤ ብልኁንም ምትሀተኛ ይነሣል።


ለዓመፀኛ ቤት እንዲህ በል፦ እነዚህ ነገሮች ምን እንደ ሆኑ አታውቁምን? በላቸው። ንገራቸው፦ እነሆ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ ንጉሥዋንና ልዑሎችዋን ወሰደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ባቢሎን አመጣቸው።


ከንጉሣውያን ቤተሰብ አንዱን ዘር ወስዶ ከእርሱ ቃል ኪዳን ጋር አደረገ፥ አማለውም፥ የምድሪቱንም አለቆች ወሰደ፤


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዱ በስዕሉ ቤት በጨለማ የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱም፦ “ጌታ አያየንም፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ብለዋልና።”


እኔም እየሰማሁ ለሌሎቹ፦ እርሱን ተከትላችሁ በከተማይቱ መካከል እለፉ ግደሉም፥ ዓይናችሁ አይራራ፥ አትዘኑም፤


ፈራጅንም ከመካከልዋ አጠፋለሁ፥ ከእርሱም ጋር አለቆችዋን ሁሉ እገድላለሁ፥” ይላል ጌታ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች