Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 27:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የምሥራቅ ነፋስ እንደሚነፍስበት ቀን በጠንካራ ዐውሎ አስወገዳቸው፤ በጦርነት ሰደዳቸው፥ ቀሰፋቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በጦርነትና በስደት ተፋለምሃት፤ የምሥራቅ ነፋስ እንደሚነፍስበት ቀን፣ በብርቱ ዐውሎ ነፋስ አሳደድሃት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር ሕዝቡን ወደ ምርኮ እንዲሰደዱ በማድረግ ቀጣቸው፤ እንደ ኀይለኛ የምሥራቅ ዐውሎ ነፋስም አባረራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በጠ​ብና በን​ቀት ይሰ​ዳ​ቸ​ዋል፤ በቍ​ጣና በክፉ መን​ፈስ ትገ​ሥ​ጻ​ቸው ዘንድ ትጀ​ም​ራ​ለ​ህን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የምሥራቅ ነፋስ እንደሚነፍስበት ቀን በጠንካራ ዐውሎ አስወገዳቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 27:8
33 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ! እውነትና ጽኑ ፍቅር አምላክንም ማወቅ በምድሪቱ ስለ ሌለ ጌታ በምድሪቱ ላይ ከሚኖሩ ጋር ሙግት አለውና የጌታን ቃል ስሙ።


ነገር ግን በቁጣ ተነቀለች፥ ወደ መሬትም ተጣለች፤ የምሥራቅ ነፋስ ፍሬዋን አደረቀ፤ ብርቱ ቅርንጫፎቿም ተሰበሩና ደረቁ፤ እሳትም በላቸው።


አቤቱ! ገሥጸኝ፤ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቁጣ አይሁን።


በዚያ ጊዜ ለዚህ ሕዝብና ለኢየሩሳሌም፦ “ለማበጠር ወይም ለማጥራት ሳይሆን የሚያቃጥል ነፋስ በምድረ በዳ ካሉ ከተራቈቱ ኮረብቶች ወደ ወገኔ ሴት ልጅ ይመጣል፤


አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና ብታዝኑም እንኳን፥ እጅግም ደስ ይላችኋል።


በወንድሞቹ መካከል ፍሬያማ ቢሆንም እንኳ የምሥራቅ ነፋስ ይመጣል፥ የጌታ ነፋስ ከምድረበዳ ይመጣል፤ ፈሳሹንም ይጠፋል፥ ምንጩንም ይደርቃል፥ የተከበሩ ዕቃዎች ሁሉ ያሉበትን መዝገብ ይበዘብዛል።


አንተ ባርያዬ ያዕቆብ ሆይ! እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፥ ይላል ጌታ፤ አንተንም እንድትሰደድ ያደረግኹባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁና፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ እንደጥፋትህ መጠን እቀጣሃለሁ እንጂ ያለ ቅጣት ከቶ አልተውህም።”


አንተን ለማዳን ከአንተ ጋር ነኝና፥ ይላል ጌታ፤ አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ እንደጥፋትህ መጠን እቀጣሃለሁ እንጂ ያለ ቅጣት ከቶ አልተውህም።


ጌታም እንዲህ ይላል፦ “ምድር ሁሉ ባድማ ትሆናለች፥ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋትም።


በሰው ከሚደርሰው ፈተና በቀር ምንም አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፤ መታገሥ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫ መንገድ ደግሞ ያዘጋጅላችኋል።


መንፈስም የፈጠርሁትም ነፍስ ከፊቴ እንዳይዝል ለዘለዓለም አልጣላም፥ ሁልጊዜም አልቈጣም።


ጥቂት ጊዜ ተውሁሽ፥ በታላቅም ምሕረት እሰበስብሻለሁ።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ እናታችሁን የፈታሁበት የፍቺዋ ጽሕፈት የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለየትኛው ነው? እነሆ፥ ስለ ኃጢአታችሁ ተሸጣችኋል፥ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈታለች።


ጌታ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ የሚያደርገውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፤ እንዲህ ይላል የአሦርን ንጉሥ ስለ ልቡ ትዕቢትና ስለ ንቀት አመለካከቱ እቀጣዋለሁ፤


ለምን ዳግመኛ ትመታላችሁ? ለምንስ በዐመፅ ትጸናላችሁ? ራሳችሁ በሙሉ ታሞአል፤ ልባችሁ ሁሉ ታውኮአል።


ፍጥረታችንን እርሱ ያውቃልና፥ እኛ አፈር እንደ ሆንን ያስታውሳል።


እርሱ ግን ርኅሩኅ ነው፥ በደላቸውንም ይቅር አላቸው፥ አላጠፋቸውምም፥ ከቁጣውም መመለስን አበዛ፥ መዓቱንም ሁሉ አላቃጠለም።


የምድር ትሑታንን ያድን ዘንድ እግዚአብሔር ለፍርድ በተነሣ ጊዜ።


ለሰንበት መታሰቢያ፥ የዳዊት መዝሙር።


ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች ስለ ስምንተኛ፥ የዳዊት መዝሙር።


በታላቅ ኃይሉ ከእኔ ጋር ይምዋገት ነበርን? ይልቁንም! ማዳመጥ ይበቃው ነበር።


ሁልጊዜም አይከስም፥ ለዘለዓለምም አይቈጣም።


ጽድቅን የሚያደርገውን፥ በመንገዶችህም የሚያስቡህን ትገናኛቸዋለህ። እኛ ኃጢአት ሠራን፤ እነሆ፥ አንተ ተቈጥተህ ነበር፤ ፊትህን ስለሰወርክብን እኛ ተሳሳትን።


ካፍ። ጌታ ለዘለዓለም አይጥልምና፥


ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራልና፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች