ኢሳይያስ 27:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፥ እስራኤልም ያቈጠቁጣል፥ ያብባልም፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 በሚመጡት ቀናት ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፤ እስራኤልም ያቈጠቍጣል፣ ያብባልም፤ በፍሬአቸውም ምድርን ሁሉ ይሞላሉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 በሚመጡት ዘመናት የያዕቆብ ዘር የሆኑ የእስራኤል ሕዝብ እንደ ወይን ግንድ ሥር ይሰዳሉ፤ አብበውም ያፈራሉ፤ ፍሬአቸውም ምድርን ይሞላል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 በሚመጣው ዘመን የያዕቆብ ልጆች ሥር ይሰድዳሉ፤ እስራኤልም ያብባል፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፥ እስራኤልም ያብባል ይጨበጭብማል፥ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ። ምዕራፉን ተመልከት |