Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 24:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ምድርም አለቀሰች ረገፈችም፤ ዓለም ደከመች ረገፈችም፤ የምድርም ታላላቅ ሕዝቦች ዛሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ምድር ትደርቃለች፤ ትረግፋለች፤ ዓለም ትዝላለች፤ ትረግፋለች፤ የምድርም መሳፍንት ይዝላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ምድሪቱ እጅግ ደርቃ ልምላሜዋ ሁሉ ይጠወልጋል፤ የምድርም ታላላቅ ሰዎች ይደክማሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ምድ​ርም አለ​ቀ​ሰች፤ ጠፋ​ችም፤ ዓለም ተገ​ለ​በ​ጠች፤ የም​ድ​ርም ታላ​ላ​ቆች አለ​ቀሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ምድርም አለቀሰች ረገፈችም፥ ዓለም ደከመች ረገፈችም፥ የምድርም ሕዝብ ታላላቆች ደከሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 24:4
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያም ቀን እንደዚህ ይሆናል፤ ጌታ በከፍታ ያለውን ሠራዊት በከፍታ ላይ፥ በምድርም ያሉትን ነገሥታት በምድር ላይ ይቀጣቸዋል።


ምድር ፈጽሞ ባድማ ትሆናለች፤ ፈጽማም ትበላሻለች፤ ጌታ ይህን ቃል ተናግሮአል።


ለኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል ለሆነች፥ በወይን ጠጅ ለተሸነፉ፥ በለምለሙ ሸለቆአቸው ራስ ላይ ላለችም ለረገፈች ለክብሩ ጌጥ አበባ ወዮላት!


የጽዮን ደጆች ያዝናሉ፤ ያለቅሳሉም፤ እርሷም ተረስታ በመሬት ላይ ትቀመጣለች።


ምድሪቱ አለቀሰች ከሳችም፤ ሊባኖስ አፈረ ጠወለገም፤ ሳሮን እንደ ምድረ በዳ ሆነ፤ ባሳንና ቀርሜሎስ ቅጠላቸውን አረገፉ።


ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።


ምድሪቱ የምታለቅሰው፥ የአገሩ እጽዋት ሁሉ የሚደርቀው እስከ መቼ ነው? የተቀመጡባት ሰዎች፦ “ፍጻሜያችንን አያይም” ብለዋልና ስለ ክፋታቸው እንስሶችና ወፎች ተጠራርገው ጠፍተዋል።


ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፥ በላይም ሰማይ ይጠቁራል፤ ተናግሬአለሁና፥ አስቤአለሁም፤ አልጸጸትም ከእርሱም አልመለስም።”


ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓልም የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ፥ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል ካህናቶችዋም እየጮኹ ያለቅሳሉ፥ ድንግሎችዋም ተጨነቁ እርሷም በምሬት አለች።


ስለዚህ ምድሪቱ ታለቅሳለች፥ በእርሷም የሚቀመጡ ሁሉ ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች ጋር በድካም ይዝላሉ፤ የባሕሩም ዓሦች እንኳ ያልቃሉ።


እህሉ ጠፍቶአልና፥ ወይኑም ደርቆአልና፥ ዘይቱም ጐድሎአልና እርሻው ምድረ በዳ ሆኖአል፥ ምድሪቱም አልቅሳለች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች