ኢሳይያስ 24:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 በሕዝቡ ላይ የሚሆነው እንዲሁ ካህኑ ላይ ይሆናል፤ በአገልጋዩ ላይ የሚሆነው እንዲሁ በአስተዳዳሪው፥ በአገልጋይቱም የሚሆነው እንዲሁ በእመቤትዋ፥ በሸማቹ ላይ የሚሆነው እንዲሁ በሻጩ፥ በአበዳሪው የሚሆነው እንዲሁ በተበዳሪው፥ በዕዳ አስከፋዩም የሚሆነው እንዲሁ በዕዳ ከፋዩ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ነገሩ ሁሉ አንድ ዐይነት ይሆናል፤ በሕዝቡ ላይ የሚሆነው በካህኑ፣ በአገልጋዩ ላይ የሚሆነው በጌታው፣ በአገልጋይዋ ላይ የሚሆነው በእመቤቷ፣ በገዥው ላይ የሚሆነው በሻጩ፣ በተበዳሪው ላይ የሚሆነው በአበዳሪው፣ በብድር ከፋይ ላይ የሚሆነው በብድር ሰጪው ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 የሰው ሁሉ ዕድል አንድ ዐይነት ይሆናል፤ ካህናትና ሕዝቡ፥ አገልጋዮችና አሳዳሪዎቻቸው፥ እመቤቲቱና አገልጋይቱ፥ ገዢዎችና ሻጮች፥ አበዳሪዎችና ተበዳሪዎች፥ ዕዳ ከፋይና ዕዳ አስከፋይ በአንድነት ይጠፋሉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ሕዝቡ እንደ ካህኑ፥ ባሪያውም እንደ ጌታው ባሪያይቱም እንደ እመቤቷ፥ የሚሸጠውም እንደሚገዛው፥ ተበዳሪውም እንደ አበዳሪው፥ ዕዳ ከፋዩም እንደ ዕዳ አስከፋዩ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 እንደ ሕዝቡም እንዲሁ ካህኑ፥ እንደ ባሪያውም እንዲሁ ጌታው፥ እንደ ባሪያይቱም እንዲሁ እመቤትዋ፥ እንደሚገዛም እንዲሁ የሚሸጠው፥ እንደ አበዳሪውም እንዲሁ ተበዳሪው፥ እንደ ዕዳ አስከፋዩም እንዲሁ ዕዳ ከፋዩ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከት |