Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 23:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አክሊል በተቀዳጀች፥ ነጋዴዎችዋ መሳፍንት በሆኑ፥ በምድር የከበሩ ሻጮችና ለዋጮች በነበሯት፥ በጢሮስ ላይ ይህን ያሰበ ማን ነበር?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 አክሊል በምታቀዳጀዋ፣ ነጋዴዎቿ መሳፍንት በሆኑ፣ በምድር የከበሩ ሻጮችና ለዋጮች በነበሯት፣ በጢሮስ ላይ ይህን ያሰበ ማን ነበር?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ዘውድን ታቀዳጅ በነበረችው ከተማ፥ ልዑላን የሆኑና በዓለም የተከበሩ ነጋዴዎች በነበርዋት በጢሮስ ላይ ይህን ሁሉ ያቀደ ማነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በጢ​ሮስ ላይ ይህን የመ​ከረ ማን ነው? እር​ስዋ ከሁሉ የም​ት​ሻ​ልና የም​ት​በ​ልጥ አይ​ደ​ለ​ች​ምን? ነጋ​ዴ​ዎ​ችዋ የከ​በሩ የም​ድር አለ​ቆች ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አክሊል ባስጫነች ከተማ በጢሮስ ላይ ይህን የወሰነ ማን ነው? ነጋዴዎችዋ አለቆች ናቸው፥ በእርስዋ የሚሸጡና የሚለወጡ የምድር ክቡራን ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 23:8
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲህም ይል ነበር፤ “የጦር አዛዦቹ በሙሉ ነገሥታት አይደሉምን?


ስለ ሰረገሎችና ስለ ፈረሰኞች በግብጽ ስትታመን፥ ከአለቃዬ ባርያዎች የሚያንሰውን የአንዱን አለቃ ፊት ለመቃወም እንዴት ይቻልሃል?


ሀብትሽን ይዘርፋሉ፥ ሸቀጣ ሸቀጥሽንም ይበዘብዛሉ፤ ቅጥርሽን ያፈርሳሉ፥ የተዋቡ ቤቶችሽን ያጠፋሉ፤ ድንጋይሽን፥ እንጨትሽንና አፈርሽን በውኆች መካከል ያስቀምጣሉ።


ነጋዴዎችሽን ከሰማይ ከዋክብት ይልቅ አበዛሽ፤ አንበጣ ተዘረጋና በረረ።


ጢሮስም ምሽግን ለራስዋ ሠርታለች፥ ብሩንም እንደ አፈር ወርቁንም እንደ መንገድ ጭቃ አከማችታለች።


የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፤ የሙሽራውና የሙሽራይቱም ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፤ በአስማትሽም አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና።”


ስለዚህም ሞትና ኀዘን፥ ራብም የሆኑት መቅሰፍቶችዋ በአንድ ቀን ይመጣሉ፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች