ኢሳይያስ 23:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ስለ ጢሮስ የተነገረ ትንቢት። እናንተ የተርሴስ መርከቦች ሆይ፥ ወደባቹህ ፈርሷልና አልቅሱ፤ ዜናው ከኪትም ምድር ደርሷችኋል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ስለ ጢሮስ የተነገረ ንግር፤ የተርሴስ መርከቦች ሆይ፤ ዋይ በሉ! ጢሮስ ተደምስሳለችና፣ ያለ ቤትና ያለ ወደብ ቀርታለች። ከቆጵሮስ ምድር፣ ዜናው ወጥቶላቸዋል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ስለ ጢሮስ ከተማ የተነገረ የትንቢት ቃል ይህ ነው፤ ጢሮስና ቤትዋ ወይም ወደብዋ የፈራረሱ ስለ ሆነ እናንተ የተርሴስ መርከቦች እሪ በሉ፤ ከቆጵሮስ ስትመለሱ የሚጠብቃችሁ ወሬ ይኸው ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ስለ ጢሮስ የተነገረ ትንቢት። የኬልቀዶን መርከቦች ሆይ፥ አልቅሱ፤ ጠፍተዋልና፤ እንግዲህም ከኬጤዎን ሀገር አይመጡምና ማርከውም ይወስዱአቸዋልና። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ስለ ጢሮስ የተነገረ ሸክም። የተርሴስ መርከቦች ሆይ፥ አልቅሱ፥ ፈርሶአልና ቤት የለም፥ መግባትም የለም፥ ከኪትም አገር ጀምሮ ተገልጦላቸዋል። ምዕራፉን ተመልከት |