Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 22:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ኤላምም ከሰረገለኞችና ከፈረሰኞች ጋር ሆኖ አፎቱን ተሸከመ፥ ቂርም ጋሻውን አነገበ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ኤላም የፍላጻ ሰገባ፣ ፈረሷንና ሠረገላዋን አዘጋጀች፤ ቂርም ጋሻዋን አነገበች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የዔላም አገር ወታደሮች በሠረገላና በፈረስ ተቀምጠው ቀስትና ፍላጻ አንግበው መጡ፤ የቂር ወታደሮች ጋሻቸውን አዘጋጅተዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የኤ​ላ​ምም ሰዎች አፎ​ታ​ቸ​ውን ተሸ​ከሙ፤ በፈ​ረስ የተ​ቀ​መ​ጡና አር​በ​ኞች ሰዎች፥ የአ​ር​በ​ኞ​ችም ሠራ​ዊት ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ኤላምም ከሰረገለኞችና ከፈረሰኞች ጋር ሆኖ አፎቱን ተሸከመ፥ ቂርም ጋሻውን ገለጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 22:6
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የአካዝን ጥያቄ በመቀበል ቲግላት ፐሌሴር ዘምቶ ደማስቆን በቁጥጥሩ ሥር አደረገ፤ ንጉሥ ረጺንንም ገደለ፤ ሕዝቡንም ማርኮ ቂር ተብላ ወደምትጠራው ስፍራ ወሰደው።


አስጨናቂ ራእይ ተነገረኝ፤ ከሓዲ አሳልፎ ይሰጣል፤ አጥፊውም ያጠፋል። ኤላም ሆይ፥ ውጪ! ሜዶን ሆይ፥ ክበቢ፤ ጭንቀቷን ሁሉ አጠፋለሁ።


“የእስራኤል ልጆች ሆይ! እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን?” ይላል ጌታ። “እስራኤልን ከግብጽ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?


የደማስቆንም መቀርቀሪያ እሰብራለሁ፥ ነዋሪዎችዋንም ከአዌን ሸለቆ፥ በትረ መንግሥት የያዘውንም ከዔደን ቤት አጠፋለሁ፤ የሶርያም ሕዝብ ተማርከው ወደ ቂር ይሄዳሉ፥” ይላል ጌታ።


የሞዓብ ኤር በሌሊት ፈርሶ ጠፋ፤ ቂር የሚባልም የሞዓብ ምሽግ በሌሊት ፈርሶ ጠፋ።


የሴም ልጆች፦ ዔላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ እና አራም ናቸው።


ምርጦቹም ሸለቆችሽ ሠረገሎች ሞሉባቸው፤ ፈረሰኞችም በሮች ላይ ቆመዋል።


በዚያን ቀን፤ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደገና የተረፈውን የሕዝቡን ትሩፍ ከአሦር፤ ከታችኛው ግብጽ፤ ከላይኛው ግብጽ፤ ከኢትዮጵያ፤ ከኤላም፤ ከባቢሎን፤ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች