Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 22:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ከሠራዊት ከጌታ በራእይ ሸለቆ ውስጥ የድንጋጤና የመረገጥ፥ ግራ የመጋባት፥ የቅጥር መፍረስና ወደ ተራራ ለእርዳታ የሚጮኽበት ቀን ሆኖአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ጌታ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በራእይ ሸለቆ፣ የመጯጯኺያ፣ የመረገጥና የሽብር፣ ቅጥሮችን የማፈራረስ፣ ወደ ተራሮችም የሚጮኽበት ቀን አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ይህ በራእይ ሸለቆ የጭንቅ፥ የመረገጥ፥ የሽብር ጊዜ ነው፤ ይህ ሁሉ በእኛ ላይ እንዲፈጸም የፈቀደው የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው፤ የከተማችን ቅጽሮች ፈራርሰው ወድቀዋል፤ ርዳታ ለማግኘት የሚደረገውም ጩኸት እስከ ተራራዎች በማስተጋባት ላይ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሁ​ከ​ትና የጥ​ፋት፥ የመ​ረ​ገ​ጥና የስ​ብ​ራ​ትም ቀን በጽ​ዮን ሸለቆ ውስጥ ሆኖ​አል። ታና​ሹና ታላ​ቁም ሸሽ​ተው በተ​ራራ ላይ ይቅ​በ​ዘ​በ​ዛሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ የድንጋጤና የመረገጥ የድብልቅልቅም ቀን፥ የቅጥርን መፍረስ ወደ ተራራ መጮኽ በራእይ ሸለቆ ውስጥ ሆኖአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 22:5
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለኢሳይያስም እንዲነግሩት የላከው መልእክት ከዚህ የሚከተለው ነው፦ “ዛሬ የታላቅ መከራ ቀን ነው፤ የሚያሳፍር ቅጣትና ውርደት እየደረሰብን ነው፤ የምትወልድበት ጊዜ ደርሶ ለማማጥ አቅም እንዳነሣት ሴት ሆነናል፤


በክብር ዘቡ አዛዥ ሥር የነበሩት የባቢሎናውያን ወታደሮች የኢየሩሳሌም ዙሪያ አጥር


ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፤ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፤ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፤ አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፤ በሚያስቆጣኝም ሕዝብ ላይ እሰደዋለሁ።


ስለ ራእይ ሸለቆ የተነገረ ራእይ። እናንተ ሁላችሁ ወደ ሰገነት መውጣታችሁ ምን ማለት ነው?


የጌታም እጅ በዚህ ተራራ ላይ ታርፋለች፤ ጭድም በጭቃ ውስጥ እንደሚረገጥ እንዲሁ ሞዓብ በሥፍራው ይረገጣል።


እነርሱም፦ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል ለመውለድም ብርታቱ የለም።


እንግዲህ በወይኔ ቦታ ምን እንደማደርግ ልንገራችሁ፤ ዐጥሩን እነቅላለሁ፤ ለጥፋት ይጋለጣል፤ ግንቡንም አፈርሳለሁ፤ መረጋገጫም ይሆናል።


“መጥመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፥ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፤ በቁጣዬ ረገጥኋቸው በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፤ ደማቸውም በልብሴ ላይ ተረጭቶአል፥ ልብሴንም ሁሉ አሳድፌአለሁ።


በቁጣዬም አሕዛብን ረገጥሁ በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፥ ደማቸውንም ምድር ላይ አፈሰስኩት።”


ወዮ! ያ ቀን ታላቅ ነውና፥ እርሱንም የሚመስል የለምና፤ ያ የያዕቆብ መከራ ዘመን ነው፥ ነገር ግን ከእርሱ ይድናል።


ሄ። ስለ ኃጢአትዋ ብዛት እግዚአብሔር አስጨንቆአታልና አስጨናቂዎችዋ ራስ ሆኑ ጠላቶችዋም ተከናወነላቸው፥ ሕፃናቶችዋ በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል።


ቤት። ጌታ የያዕቆብን ማደሪያዎች ሁሉ ዋጠ፥ አልራራምም፥ በመዓቱ የይሁዳን ሴት ልጅ አምቦች አፈረሰ፥ ወደ ምድርም አወረዳቸው መንግሥቱንና አለቆችዋን አረከሰ።


ሔት። እግዚአብሔር የጽዮንን ሴት ልጅ ቅጥር ያፈርስ ዘንድ አሰበ፥ የመለኪያውን ገመድ ዘረጋ፥ እጁን ከማጥፋት አልመለሰም፥ ምሽጉና ቅጥሩ እንዲያለቅሱ አደረገ፥ በአንድነት ደከሙ።


በምድር የምትኖር ሆይ፥ ፍጻሜህ ወደ አንተ መጥቷል፥ ጊዜው መጥቷል፥ ቀኑ ቀርቧል፥ የሽብር ነው እንጂ በተራራ ላይ ያለ እልልታ አይደለም።


የእስራኤል ኃጢአት የሆኑት የአዌን የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ እሾኽና አሜከላ በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላል፤ እነርሱም ተራሮችን፦ “ሸፍኑን!” ኮረብቶችንም፦ “ውደቁብን!” ይሉአቸዋል።


ከእነርሱ የተሻለ የተባለው እንደ አሜከላ ነው፥ ቅን የተባለው እንደ ኩርንችት ነው፤ ጠባቂዎችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቷል፤ መሸበራቸውም አሁን ይሆናል።


ያ ቀን የመዓት ቀን የጭንቀትና የሥቃይ ቀን፥ የጥፋትና የመፍረስ ቀን፥ የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን፥


በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉት ወደ ተራሮች ይሽሹ፤


በዚያን ጊዜ ተራራዎችን ‘በላያችን ውደቁ፤’ ኮረብቶችንም ‘ሰውሩን፤’ ማለት ይጀምራሉ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች