ኢሳይያስ 22:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ጠቅልሎም ያንከባልልሃል፥ ወደ ሰፊይቱም ምድር እንደ ኳስ ይወረውርሃል፤ አቤት፥ አንተ የጌታህ ቤት እፍረት! በዚያም ትሞታለህ፥ በዚያም የክብርህ ሠረገላዎች ይቀራሉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 አዙሮ አዙሮ እንደ ሩር አጡዞ፣ ወደ ሰፊ አገር ይወነጭፍሃል፤ አንተ የጌታህ ቤት ዕፍረት! በዚያ ትሞታለህ፤ የክብር ሠረገሎችህም እዚያ ይቀራሉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 እርሱም ወደምትሞትበትና ሠረገሎችህም ቆመው ወደሚቀሩበት ቦታ እንደ ኳስ ጠቅልሎ ወደ ሰፊው ሜዳ ይወረውርሃል፤ ለጌቶችህም ኀፍረት ትሆናለህ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ወደ መከራ ሀገር ይጥልሃል፤ በዚያም ትሞታለህ፤ ያማረ ሰረገላህንም ያጐሰቍለዋል፤ የአለቃህም ቤት ይረገጣል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 ጠቅልሎም ያንከባልልሃል ወደ ሰፊይቱም ምድር እንደ ኳስ ይጥልሃል፥ አንተ የጌታህ ቤት እፍረት! በዚያ ትሞታለህ በዚያም የክብርህ ሰረገላዎች ይሆናሉ። ምዕራፉን ተመልከት |