ኢሳይያስ 22:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ነገር ግን እናንተ፦ “ነገ እንሞታለንና እንብላ እንጠጣም” በማለት እነሆም፥ በሐሤትና በደስታ በሬንና በጉንም ስታርዱ፥ ሥጋንም ስትበሉ፥ የወይን ጠጅንም ስትጠጡ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ነገር ግን እነሆ፤ ደስታና ሐሤት፣ ፍሪዳ መጣልና ሙክት ማረድ፣ ሥጋ መብላትና የወይን ጠጅ መጠጣት አለ! “ነገ ስለምንሞት፣ እንብላ፤ እንጠጣ!” አላችሁ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 እናንተ ግን ጥሪውን በመቀበል ፈንታ በዓል አደረጋችሁ፤ የምትበሉትንም በግና በሬ ዐረዳችሁ፤ ወይን ጠጅም ጠጥታችሁ “ነገ እንሞታለን ዛሬ እንብላ እንጠጣ!” አላችሁ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 እነሆም፥ በዓልን፥ ደስታንና ሐሴትን አደረጋችሁ፤ በሬዎችንና በጎችንም አረዳችሁ፤ “ነገ እንሞታለን፤ እንብላ፤ እንጠጣም፤” እያላችሁ ሥጋን በላችሁ፤ ወይንንም ጠጣችሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 እነሆም፥ ሐሤትና ደስታ በሬንና በጉንም ማረድ ሥጋንም መብላት የወይን ጠጅንም መጠጣት ሆነዋል፥ እናንተ፦ ነገ እንሞታለንና እንብላ እንጠጣ ብላችኋል። ምዕራፉን ተመልከት |