Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 21:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ስለ አረብ የተነገረ ሸክም። የድዳናውያን ነጋዴዎች ሆይ፥ በዓረብ ዱር ወስጥ ታድራላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ስለ ዐረብ አገር የተነገረ ንግር፤ እናንተ በዐረብ ዱር የምትሰፍሩ፣ የድዳን ሲራራ ነጋዴዎች፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ስለ ዐረብ አገር የተነገረውም ቃል ይህ ነው፤ ከጭነት ግመሎቻችሁ ጋር በዐረብ በረሓ የምትሰፍሩ እናንተ የደዳን ሕዝብ ሆይ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሌሊ​ትም በዲ​ዳ​ና​ው​ያን ጎዳና በዛ​ፎች ውስጥ ታድ​ራ​ለህ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ስለ ዓረብ የተነገረ ሸክም። የድዳናውያን ነጋዴዎች ሆይ፥ በዓረብ ዱር ወስጥ ታድራላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 21:13
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የድዳን ልጆችም ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ይለውጡ ዘንድ የዝሆን ጥርስና ዞጲ አመጡልሽ።


የአብርሃምም ቊባት የኬጡራ ልጆች፤ ዚምራን፥ ዮቅሻን፥ ሜዳን፥ ምድያም፥ የሽቦቅ፥ ሹሐን ናቸው። የዮቅሻንም ልጆች፤ ሳባና ድዳን ናቸው።


ዮቅሻንም ሳባንና ድዳንን ወለደ። የድዳንም ልጆች አሹራውያን፥ ለጡሻውያንና፥ ለኡማውያን ናቸው።


ስለዚህ አጋር በዓረብ አገር ያለችው ሲና ተራራ ናት፤ አሁን ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፥ ከልጆችዋ ጋር በባርነት ናትና።


በዘመናት ሁሉ የሚቀመጥባት አይኖርም፤ የሚቀመጥባትም የለም ዐረብ በዚያ ድንኳኑን አይተክልም፤ እረኛም መንጋውን በዚያ አያሳርፍም።


የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ባቢሎን ያየው ትንቢት፤


የኩሽም ልጆች፤ ሴባ፥ ሐዊላ፥ ሰብታ፥ ራዕማ፥ ሰብቃታ ናቸው። የራዕማም ልጆች፤ ሳባ፥ ድዳን ናቸው።


ይህም ሁሉ ነጋዴዎች ከሚከፍሉት ቀረጥ፥ ከንግድ ከሚገኘው ትርፍ፥ እንዲሁም ከዐረብ ነገሥታትና ከእስራኤል ክፍላተ ሀገር አስተዳዳሪዎች ከሚገባለት ግብር ጋር ተጨማሪ ነበር።


የኩሽ ልጆች፦ ሳባ፥ ሐዊላ፥ ሳብታ፥ ራዕማ እና ሳብተካ ናቸው። የራማ ልጆች፥ ሳባ እና ደዳን ናቸው።


ጉበኛውም፦ “ይነጋል ደግሞም ይመሻል፤ ትጠይቁ ዘንድ ብትወድዱ ጠይቁ፤ ተመልሳችሁም ኑ” አለ።


የዔሳውን ጥፋት እርሱን በምጐበኝበት ጊዜ አመጣበታለሁና፥ እናንተ በድዳን የምትኖሩ ሆይ! ሽሹ፥ ወደ ኋላ ተመለሱ፥ በጥልቅም ውስጥ ተቀመጡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች