ኢሳይያስ 19:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፤ በዐባይ ወንዝ ላይ መንጠቆአቸውን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፤ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት በድካም ይዝላሉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ዓሣ አጥማጆች ያዝናሉ፤ በአባይ ወንዝ ላይ መንጠቋቸውን የሚወረውሩ ሁሉ ያለቅሳሉ፤ በውሃ ላይ መረባቸውን የሚጥሉ ሁሉ፣ ጕልበታቸው ይዝላል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 መንጠቆአቸውን ወደ አባይ ወንዝ የሚጥሉ ዓሣ አጥማጆች ያዝናሉ፤ ያለቅሳሉም፤ መረቦቻቸውንም በውሃ ላይ የሚዘረጉ ተስፋ ይቈርጣሉ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፤ በዓባይም ወንዝ መቃጥን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፤ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት ያለቅሳሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፥ በዓባይም ወንዝ መቃጥን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፥ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት ይዝላሉ። ምዕራፉን ተመልከት |