ኢሳይያስ 19:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 በዚያ ቀን እስራኤል፤ ከግብጽና ከአሦር ጋር የምድር በረከት ለመሆን በሦስተኛነት ትቈጠራለች። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 በዚያ ቀን እስራኤል፣ ከግብጽና ከአሦር ጋራ የምድር በረከት ለመሆን በሦስተኛነት ትቈጠራለች። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 በዚያን ጊዜ እስራኤል ከግብጽና ከአሦር ጋር ተደምራ ሦስተኛ አገር ትሆናለች፤ እነዚህም ሦስት ሕዝቦች በዓለም መካከል በረከት ይሆናሉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 በዚያም ወራት እስራኤል ለግብፅና ለአሦር ሦስተኛ ይሆናል፤ በምድርም መካከል በረከት ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24-25 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦ ሕዝቤ ግብጽ፥ የእጄም ሥራ አሦር፥ ርስቴም እስራኤል የተባረከ ይሁን ብሎ ይባርካቸዋልና በዚያ ቀን እስራኤል ለግብጽና ለአሦር ሦስተኛ ይሆናል፥ በምድርም መካከል በረከት ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከት |