Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 17:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አጫጅ የቆመውን እህል በእጁ ሰብስቦ ዛላውን እንደሚያጭድ፥ በራፋይም ሸለቆ እንደሚለቀም ቃርሚያ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ዐጫጅ የቆመውን ሰብል ሰብስቦ፣ ዛላውንም በክንዱ እንደሚያጭድ፣ ይህም በራፋይም ሸለቆ እንደሚለቀም ቃርሚያ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እስራኤል እህሉ ታጭዶ መከር ከተሰበሰበ በኋላ ባዶውን እንደሚቀር እርሻ ትሆናለች፤ ከመከር በኋላ የተራቈተ የራፋይምን ሸለቆም ትመስላለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 አጫጅ የቆ​መ​ውን እህል ሰብ​ስቦ ዛላ​ውን እን​ደ​ሚ​ያ​ጭድ ይሆ​ናል፤ በሸ​ለቆ እሸ​ትን እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ስ​ብም እን​ዲሁ ይሆ​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 አጫጅ የቆመውን እህል በእጁ ሰብስቦ ዛላውን እንደሚያጭድ ይሆናል፥ በራፋይም ሸለቆ ቃርሚያ እንደሚለቅም ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 17:5
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፍልስጥኤማውያንም መጥተው በራፋይም ሸለቆ ተበታትነው ሰፈሩ።


ፍልስጥኤማውያን እንደገና መጥተው በራፋይም ሸለቆ ተበታትነው ሰፈሩ።


ደረቅ ሣር በታጨደ ጊዜ፥ አዲስ ለምለም በታየ ጊዜ፥ ከተራራውም ቡቃያ በተሰበሰበ ጊዜ


በተከልክበት ቀን እንዲበቅል፥ በዘራህበት ማግስት እንዲያብብ ብታደርግ እንኳን፥ ነገር ግን በኀዘንና በብርቱ ደዌ ቀን መከሩ እንዳልነበር ይሆናል።


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “የባቢሎን ሴት ልጅ በመረገጥ ላይ እንዳለ ዐውድማ ነች፤ ጥቂት ቈይታ የመከር ጊዜ ይደርስባታል።”


ተናገር፥ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘የሰውም ሬሳ እንደ ጉድፍ በእርሻ ላይ፥ ማንምም እንደማይሰበስበው ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል።’ ”


ይሁዳ ሆይ! የሕዝቤን ምርኮ በምመልስበት ጊዜ ለአንተ ደግሞ መከር ተወስኖልሃል።


መከሩ ደርሶአልና ማጭድ ስደዱ፥ መጥመቂያውም ሞልቶአልና ኑ እርገጡ፥ ክፉታቸውም በዝቶአልና መጥመቂያ ሁሉ ፈርሶአል።


እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ ተዉአቸው፤ በመከር ጊዜ አጫጆቹን “አስቀድማችሁ እንክርዳዱን በእሳትም ለማቃጠል ሰብስባችሁ በየነዶው እሰሩት፤ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱት፤ እላቸዋለሁ።”


ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ ኢየሩሳሌም ወደምትባለው ወደ ኢያቡሳዊው ወደ ደቡብ ወገን ወጣ፤ ድንበሩም በራፋይም ሸለቆ ዳር በሰሜን በኩል ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በምዕራብ ወገን ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ወጣ፤


ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳለው ተራራ መጨረሻ ወረደ፥ እርሱም በራፋይም ሸለቆ በሰሜን በኩል ነው፤ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያቡስ ወገን በደቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ዓይንሮጌልም ወረደ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች