Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 17:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በተከልክበት ቀን እንዲበቅል፥ በዘራህበት ማግስት እንዲያብብ ብታደርግ እንኳን፥ ነገር ግን በኀዘንና በብርቱ ደዌ ቀን መከሩ እንዳልነበር ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በተከልህበት ቀን እንዲበቅል፣ በዘራህበትም ማግስት እንዲያብብ ብታደርግ እንኳ፣ መከሩ በደዌና በማይሽር ሕመም ቀን፣ እንዳልነበረ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በዚያው በተከላችሁት ቀን አድጎ ቢያብብ እንኳ ከቶ አታመርቱትም፤ በዚህ ፈንታ የምታመርቱት ችግርና የማይፈወስ በሽታ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ተክ​ልን በተ​ከ​ል​ህ​በት ቀን ትበ​ድ​ላ​ለህ፤ የዘ​ራ​ኸ​ውም በበ​ነ​ጋው በም​ታ​ወ​ር​ስ​በት ቀን ይበ​ቅ​ላል፤ አባ​ትም ለልጁ እን​ደ​ሚ​ያ​ወ​ርስ አን​ተም ለል​ጆ​ችህ ታወ​ር​ሳ​ለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በተከልህበት ቀን ታበቅለዋለህ፥ በነጋውም ዘርህን እንዲያብብ ታደርገዋለህ፥ ነገር ግን በኀዘንና በትካዜ ቀን መከሩ ይሸሻል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 17:11
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነፋስን ዘሩ፥ ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፤ የቆመውም እህል ዛላ የለውም፥ ከእርሱም ዱቄት አይገኝም፤ ቢገኝም እንኳ ባዕዳን ይበሉታል።


እኔ እንዳየሁት፥ ኃጢአትን የሚያርሱ፥ መከራንም የሚዘሩ ይህንኑ ያጭዳሉ።


ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሓ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቁጣ ቀን በራስህ ላይ ቁጣን ታከማቻለህ።


ኤፍሬም ተመታ፥ ሥሩም ደረቀ፥ ፍሬም አያፈራም፤ ደግሞም ቢወልዱ እንኳ እጅግ የሚወዱአቸውን የማኅፀናቸውን ፍሬ እገድላለሁ።


ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእነዚህ እጅ ይገዛሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ወድደዋል፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?


ማልዶ ያብባል፥ በሠርክም ጠውልጎና ደርቆ ይወድቃል።


ጉልበታችሁም በከንቱ ያልቃል፤ ምድራችሁም የተትረፈረፈውን ምርትዋን አትሰጥም፥ የምድሪቱም ዛፎች ፍሬያቸውን አይሰጡም።


ወይን ተክለህ ትንከባከበዋለህ፤ ነገር ግን ትል ስለሚበላው ዘለላውን አትሰበስብም ወይም ከወይኑ አትጠጣም።


አጫጅ የቆመውን እህል በእጁ ሰብስቦ ዛላውን እንደሚያጭድ፥ በራፋይም ሸለቆ እንደሚለቀም ቃርሚያ ይሆናል።


ዘሩ በምድር ውስጥ ተበላሸ፥ እህሉ ደርቆአልና ጎተራዎቹ ባዶ ናቸው፥ ጎታዎቹም ፈርሰዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች