ኢሳይያስ 16:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ከሞዓብ የተሰደዱት ከአንቺ ዘንድ ይኑሩ፤ ስደተኞቹን ከሚሳድዷቸው መሸሸጊ ሁኛቸው። የሚያስጨንቁ አልቀዋል፥ ጥፋትም ቀርቷል፤ ጨቋኞች የነበሩ ከምድር ጠፍተዋል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 የሞዓባውያን ስደተኞች ከእናንተ ጋራ ይቈዩ፤ እናንተም ከአጥፊው መጠጊያ ሁኗቸው።” የጨቋኙ ፍጻሜ ይመጣል፤ ጥፋቱ ያከትማል፤ እብሪተኛም ከምድር ገጽ ይጠፋል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 የሞአብ ስደተኞች በመካከላችሁ ይኑሩ፤ ሊያጠፉአቸው ከሚፈልጉ ወገኖች መጠጊያ ሁኑአቸው።” ጨቋኞች ከእንግዲህ ወዲያ አይኖሩም፤ ያገር መፈራረስም ያከትማል። ወራሪዎችም ይወገዳሉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ከሚከቧችሁ ጋር ጠላቶች እንዳይሆኗችሁ ከሞዓብ የተሰደዱትን ከእናንተ ጋር አታስቀምጡ፤ ሰልፈኞች አልቀዋልና፤ በሀገሪቱ ሁሉ የነበረውም አለቃ ጠፍቶአልና። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ከሞዓብ የተሰደዱት ከአንቺ ጋር ይቀመጡ፥ ከሚያጠፋቸው ፊት መጋረጃ ሁኛቸው። የሚያስጨንቁ አልቀዋል፥ ጥፋትም ቀርቷል፥ ይጨቍኑ የነበሩ ከምድር ጠፍተዋል። ምዕራፉን ተመልከት |