Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 16:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በምድረ በዳ ካለችው ከሴላ በምድር ላይ ገዢ ለሆነው ወደ ጽዮን ሴት ልጅ ተራራ የበግ ጠቦቶችን ስደዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከምድረ በዳው ማዶ ካለችው ከሴላ፣ ለምድሪቱ ገዥ፣ ወደ ጽዮን ሴት ልጅ ተራራ የበግ ጠቦት ግብር ላኩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የሞአብ ሕዝብ ሆይ! በጽዮን ተራራ ላይ ለሚገኘው ለሀገሪቱ መሪ ከሴላ በበረሓው በኩል ጠቦቶችን እጅ መንሻ አድርጋችሁ ላኩለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የጽ​ዮን ሴት ልጅ ተራራ ምድረ በዳ አይ​ደ​ለ​ች​ምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በምድር ላይ ለሰለጠነ አለቃ የበግ ጠቦቶችን በምድረ በዳ ካለችው ከሴላ ወደ ጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ስደዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 16:1
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚህ ቀን ኖብ ይደርሳሉ፤ እጃቸውን በኢየሩሳሌም ኰረብታ፤ በጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ላይ በዛቻ ነቀነቁ።


የሞዓብ ንጉሥ ሜሻዕ በግ አርቢ ነበር፤ በየዓመቱም አንድ መቶ ሺህ ጠቦትና የአንድ መቶ ሺህ በጎች ጠጉር ለእስራኤል ንጉሥ ይገብር ነበር፤


አሜስያስ “የጨው ሸለቆ” እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ዐሥር ሺህ የሚሆኑ የኤዶም ወታደሮችን ፈጀ፤ ሴላዕ ተብላ የምትጠራውንም ከተማ ይዞ “ዮቅትኤል” ብሎ ጠራት፤ እስከ አሁንም በዚሁ ስም ትጠራለች።


እንዲሁም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረገ፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፥ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር። ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት ተገዢዎች ሆኑ፤ ገበሩለትም።


ምድረ በዳውና ከተሞቹ የቄዳርም ሰዎች የሚቀመጡባቸው መንደሮች ድምፃቸውን ያንሡ፤ በሴላ የሚኖሩ እልል ይበሉ፥ በተራሮችም ራስ ላይ ሆነው ይጩኹ።


ስለዚህ በዚህ ገንዘብ ወይፈኖችን፥ አውራ በጎችንና ጠቦቶችን ከእህል ቁርባኖቻቸውና ከመጠጥ ቁርባኖቻቸው ጋር ተግተህ ግዛ፥ በኢየሩሳሌምም ባለው በአምላካችሁ ቤት መሠዊያ ላይ አቅርባቸው።


አንተ የመንጋው ግንብ ሆይ፥ የጽዮን ሴት ልጅ ምሽግ ሆይ፥ የቀደመችው ግዛት፥ የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ወደ አንተ ትገባለች።


የምድሪቱም ሕዝብ ሁሉ ይህን መባ ለእስራኤል መሪ ይሰጣሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች