ኢሳይያስ 14:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ምድርህን አጥፍተሃልና፥ ሕዝብህንም ገድለሃልና ከእነርሱ ጋር በመቃብር በአንድነት አትሆንም፤ የክፉዎች ዘር ለዘለዓለም የተጠራ አይሆንም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ከእነርሱ ጋራ በመቃብር አትሆንም፤ ምድርህን አጥፍተሃልና፤ ሕዝብህንም ፈጅተሃልና። የክፉ አድራጊዎች ዘር ፈጽሞ አይታወስም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 አንተ አገርህን አጥፍተህ፥ የገዛ ሕዝብህን ፈጅተሃል፤ ስለዚህም አንተ እንደ ሌሎች መንግሥታት መቃብር የማግኘት ዕድል አይኖርህም፤ ከክፉ ቤተሰብ መካከል የሚተርፍ ዘር አይኖርም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ንጹሕ እንዳልሆነና በደም እንደ ረከሰ ልብስ አንተም ንጹሕ አይደለህም። ምድሬን አጥፍተሃልና፥ ሕዝቤንም ገድለሃልና ክፉ ዘር አንተ እንግዲህ ለዘለዓለም አትኖርም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ምድርህን አጥፍተሃልና፥ ሕዝብህንም ገድለሃልና ከእነርሱ ጋር በመቃብር በአንድነት አትሆንም፤ የክፉዎች ዘር ለዘላለም የተጠራ አይሆንም። ምዕራፉን ተመልከት |