ኢሳይያስ 14:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 አሕዛብም ይዘው ወደ ስፍራቸው ያመጡአቸዋል፥ የእስራኤልም ቤት በእግዚአብሔር ምድር እንደ ሎሌዎችና እንደ ገረዶች አድርገው ይገዙአቸዋል፤ የማረኩአቸውን ይማርካሉ፥ አስጨናቂዎችንም ይገዛሉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 አሕዛብም ይወስዷቸዋል፤ ወደ ገዛ ስፍራቸውም ይመልሷቸዋል። የእስራኤል ቤት አሕዛብን ርስት ያደርጓቸዋል፤ በእግዚአብሔርም ምድር ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎች አድርገው ይገዟቸዋል፤ የማረኳቸውን ይማርኳቸዋል፤ የጨቈኗቸውንም ይገዟቸዋል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 የብዙ አሕዛብ መንግሥታት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው አገር እንዲመለሱ ይረዱአቸዋል፤ አሕዛብ እንደ ባሪያዎች ሆነው የእስራኤልን ሕዝብ ያገለግላሉ፤ ቀድሞ እስራኤልን ማርከው የነበሩ አሁን ደግሞ በእስራኤል እጅ ይማረካሉ፤ ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ቀድሞ ይጨቊኑአቸው የነበሩትን ሁሉ የመግዛት ሥልጣን ይኖራቸዋል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 አሕዛብም ይዘው ወደ ስፍራቸው ያመጡአቸዋል፤ የእስራኤልም ወገኖች ይካፈሏቸዋል፤ በዚያም ሀገር ይበዛሉ፤ በዚያም ወንዶች ባሮችና ሴቶች ባሮች ይሆናሉ። ማርከው የወሰዷቸውም ለእነርሱ ምርኮኞች ይሆናሉ፤ የገዙአቸውም ይገዙላቸዋል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 አሕዛብም ይዘው ወደ ስፍራቸው ያመጡአቸዋል፥ የእስራኤልም ቤት በእግዚአብሔር ምድር እንደ ሎሌዎችና እንደ ገረዶች አድርገው ይገዙአቸዋል፥ የማረኩአቸውን ይማርካሉ፥ አስጨናቂዎችንም ይገዛሉ። ምዕራፉን ተመልከት |