Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 14:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴትስ ወደ ምድር ተጣልክ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 አንተ የንጋት ልጅ፣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፤ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አንተ ቀድሞ መንግሥታትን ያዋረድህ፣ እንዴት ወደ ምድር ተጣልህ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 አንተ በሚያበራው የአጥቢያ ኮከብ የተመሰልክ የባቢሎን ንጉሥ ሆይ! እንደ ሰማይ ከፍ ካለው ክብርህ እንዴት ወደቅኽ! መንግሥታትን ሁሉ ታዋርድ ነበር፤ አሁን ግን ወደ መሬት ተጣልክ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 “አንተ በን​ጋት የሚ​ወጣ የአ​ጥ​ቢያ ኮከብ ሆይ፥ እን​ዴት ከሰ​ማይ ወደ​ቅህ! ወደ አሕ​ዛ​ብም መል​እ​ክ​ትን የላ​ክህ አንተ ሆይ፥ እን​ዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀ​ጠ​ቀ​ጥህ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴትስ ከምድር ድረስ ተቆረጥህ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 14:12
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁት።


ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እንደ ችቦም የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፤ በወንዞችና በውሃም ምንጮች ሲሶ ላይ ወደቀ።


“እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፤ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”


ደግሞም ይህን የበለጠ የሚያረጋግጥ የነቢያት ቃል አለ፤ ጎሕ እስኪቀድ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪገለጥ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚያስተውል ቃሉን ልብ በማለት መልካም ታደርጋላችሁ።


የሰማይም ሠራዊት ሁሉ ይሟሽሻሉ፤ ሰማያትም እንደ መጽሐፍ ጥቅልል ይጠቀለላሉ፤ ሠራዊታቸው ሁሉ ከወይንና ከበለስ ላይ እንደሚረግፍ ቅጠል ይረግፋል።


የንጋትንም ኮከብ እሰጠዋለሁ።


እግዚአብሔር ኃጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው፥


አምስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ከሰማይም ወደ ምድር ወድቆ የነበረ ኮከብ አየሁ፤ የጥልቁም ጉድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።


የምድር ሁሉ መዶሻ እንዴት ደቀቀ እንዴትስ ተሰበረ! ባቢሎንስ በአሕዛብ መካከል እንዴት መሣቀቅያ ሆነች!


የሰማይ ከዋክብትና ሠራዊታቸው፤ ብርሃን አይሰጡም፤ ፀሓይ ገና ከመውጣቷ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም።


ምንም እንኳ ባቢሎን ወደ ሰማይ ብትወጣ፥ የኃይልዋንም ከፍታ ብታጠናክር፥ ከእኔ ዘንድ አጥፊዎች ይመጡባታል፥ ይላል ጌታ።


አሌፍ። ጌታ በቁጣው የጽዮንን ሴት ልጅ እንደምን አደመናት! የእስራኤልን ውበት ከሰማይ ወደ ምድር ጣለ፥ በቁጣውም ቀን የእግሩን መረገጫ አላሰበም።


በአንቺ ላይ ሙሾ ያወርዳሉ፥ እንዲህም ይሉሻል፦ ከባሕር የተቀመጥሽ በባሕርም ውስጥ የጸናሽ፥ ከሚቀመጡብሽም ጋር በዙሪያሽ የሚኖሩትን ሁሉ ያስፈራሽ፥ ዝነኛ ከተማ ሆይ፥ እንዴት ጠፋሽ!


እንደ ንስር መጥቀህ ብትወጣ፥ ቤትህም በከዋክብት መካከል ቢሆን፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥ ይላል ጌታ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች