ኢሳይያስ 13:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 በተራሮች ላይ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፤ የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ! በመንግሥታትም መካከል፤ እንደ ተጨናነቀ ሕዝብ ድምፅ የሆነውን ውካታ ስሙ! የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሠራዊቱን ለጦርነት አሰልፎአል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 በተራሮች ላይ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ፤ በመንግሥታትም መካከል፣ እንደ ተጨናነቀ ሕዝብ ድምፅ የሆነውን ውካታ ስሙ! የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሰራዊቱን ለጦርነት አሰልፏል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 በተራሮች ላይ የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ፤ ይህም ጩኸት በአንድነት የተሰበሰቡ የብዙ ሕዝብ መንግሥታት ሁካታ ነው፤ የሠራዊት አምላክ ሠራዊቱን ለጦርነት እያዘጋጀ ነው፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 በተራሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ የሆነ የብዙ ሰው ድምፅ አለ። የተሰበሰቡ ነገሥታትና የአሕዛብ ድምፅም አለ። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ተዋጊዎች አሕዛብ ይመጡ ዘንድ አዘዘ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 በተራሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ የሆነ የብዙ ሰው ድምፅ አለ። የተከማቹት የአሕዛብ መንግሥታት የውካታ ጫጫታ አለ። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሠራዊትን ለሰልፍ አሰልፎአል። ምዕራፉን ተመልከት |